ወ/ሮ አበባ ገ/ህይወት ህወሓትን ከዱ

W/o Abeba Gebrehiwot. ወ/ሮ አበባ ገ/ህይወት Ethiopia Zare (ሐሙስ መጋቢት 17 ቀን 2007 ዓ.ም. March 26, 2015)፡- የአዲስ አበባ የኢህአዴግ ጽ/ቤት የድርጅት ጉዳይ ኃላፊ የነበሩት ወ/ሮ አበባ ገ/ህይወት፣ ኢህአዴግን መክዳታቸው ተሰማ። ወ/ሮ አበባ ኢህአዴግን የከዱት በቅርቡ ለስብሰባ በሄዱባት ዩናይትድ ስቴትስ ኦፍ አሜሪካ መሆኑ ታውቋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ዶ/ር ዳኛቸው አሰፋ ከአአ ዩኒቨርሲቲ ተባረሩ

"አሁን ገና ኢትዮጵያዊ ሆንኩ!" ዶ/ር ዳኛቸው
Dr. Dagnachew Assefa. ዶ/ር ዳኛቸው አሰፋ

Ethiopia Zare (ማክሰኞ መጋቢት 8 ቀን 2007 ዓ.ም. March 17, 2015)፡- በውጪ አገር ለሠላሳ ዓመታት የቆዩትና ለሰባት ዓመታት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በመምህርነት የሰሩት ዶ/ር ዳኛቸው አሰፋ ከስራ መባረራቸውን ገለጹ። ዶ/ር ዳኛቸው፣ ኢትዮጵያዊ ማለት መብቱ የሚረገጥ ማለት በመሆኑ፣ አሁን ገና ኢትዮጵያዊ ሆንኩ በማለት በጉዳዩ ላይ አስተያየታቸውን ገልጸዋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ነፍሰ ገዳዩ ጆን ኢትዮጵያ ውስጥ ጓደኛ አለው ተባለ

Ali Adorus, ዓሊ አድሮስ

Ethiopia Zare (ዓርብ መጋቢት 4 ቀን 2007፣ March 13, 2015)፡- የአይሲስ ዋንኛ አራማጅ ነው የተባለው ጆን (መሐመድ ኤምዋዚ) የቅርብ ጓደኛው እንግሊዛዊው ዓሊ አድሮስ ኢትዮጵያ ውስጥ በእስር እንደሚገኝ በተለያዩ የብዙኀን ዜና ማሰራጫዎች እየተናፈሰ ይገኛል። መሐመድ ኤምወዚ በማለት ራሱን ሰይሞ የቆየው ይህ ግለሰብ፣ የኩዌት ዝርያ የሆነ እንግሊዛዊ መሆኑ የተረጋገጠ ሲሆን፤ አንገት ቀልቶ ገዳዩ በሎንደን ከተማ ኮሌጅ ውስጥ ይማር እንደነበር ታውቋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ማሳሰቢያ ተሰጣቸው

Dr. Tedros Adhanom. ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም

Ethiopia Zare (ዓርብ መጋቢት 4 ቀን 2007፣ March 13, 2015)፡- የውጪ ጉዳይ ሚንስትሩ ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም፤ ብሪቱ ጃለታ የተባለች የ14 ዓመት ታዳጊ ወጣት የተሸለመችውን 20 ሚሊዮን የአውስትራሊያ ዶላር ለበጎ አድራጎት ሥራ አዋለች በማለት ዓይን ያወጣ ውሸት እንደዋሹ በጋዜጠኛ አበበ ገላው መረጋገጡን ተከትሎ፤ ከ10 በላይ የሆኑ የማኅበራዊ ድረገጽ ባለቤቶች አንድ ላይ በመሆን ሚንስትሩ ከዚህ አይነት ውሸት እንዲቆጠቡ ማሳሰቢያ እንዲደርሳቸው አድርገዋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አቶ አብዲ መሐመድ ኦማር አስነዋሪ መልስ ሰጡ

Abdi Mohamed Omar. አቶ አብዲ መሐመድ ኦማር

Ethiopia Zare (ዓርብ መጋቢት 4 ቀን 2007፣ March 13, 2015)፡- የሱማሌ ክልል ፕሬዝዳንት የሆኑት አቶ አብዲ መሐመድ በዋሽንግተን ዲሲ ለደረሰባቸው ተቃውሞ የሰጡት መልስ ከባለሥልጣን አንደበት የማይወጣ አስነዋሪ እንደነበረ ተገለጸ። ሥርዓቱ እንዲህ አይነት ሰዎችን ያቀፈ ነው ያሉት ታዛቢዎች ከተቃዋሚዎች ጋር የተደረገውን አንባጓሮ በቪድዮ በመቅረጽ ለህዝብ አቅርበዋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የአቶ ተፈራ ደገፌ የቀብር ስነ-ስርዓት በቫንኩቨር ተፈጸመ

አዲስ አበባ የሚገኝ ቤታቸውን ለፌስቱላ ሆስፒታል ለግሰዋል
Ato Tefera Degefes funeral የአቶ (ዶ/ር) ተፈራ ደገፌ የቀብር ስነ-ስርዓት በቫንኩቨር ተፈጸመ

Ethiopia Zare ማክሰኞ መጋቢት 01 ቀን 2007 ዓም March 10, 2015፦ የቀድሞ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ፤ የኢትዮጵያን የባንክ አገልግሎት ስርአት ካሳደጉት ሰዎች አንዱ የሆኑትና በመድህን ድርጅት፤ በሲቪል አቪየሽንና በተለያየ ሀላፊነት ሀገራውንና ህዝባቸውን ያገለገሉት አቶ ተፈራ ደገፌ (ዶክተር)፤ የቀብር ስነ-ስርአት ዛሬ ማክሰኞ መጋቢት 1 ቀን፤ 2007 ዓ.ም. በቫንኩቨር ካናዳ ተፈጸመ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በስዊድን የኢሳት እርዳታ ማስተባበሪያ ዝግጅት በተሳካ ሁኔታ ተጠናቀቀ

ESAT in Stockholm, 28 Feb. 2015ለኢሳት መዝሙር ተበረከተ

Ethiopia Zare: ቅዳሜ የካቲት 21 ቀን 2007 ዓ.ም. (ፌብሪዋሪ 28 ቀን 2015 ዓ.ም.) በስዊድን የተደረገው የኢሳት መርጃ ዝግጅት በተሳካ ሁኔታ መጠናቀቁ ተገለጸ። ዝግጅቱ ከቀኑ ሰባት ሰዓት (13፡ 00) የተጀመረ ሲሆን፣ የዕለቱን ዝግጅት የመሩት ወ/ሮ መቅደስ ወርቁ የስዊድን የኢሳት ድጋፍ ኮሚቴ ሰብሳቢ እና አቶ በረከት ንጉሱ ነበሩ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ታዋቂው የባንክ ባለሙያ፤ አቶ ተፈራ ደግፌ አጭር ታሪክ

Tefera Degefe አቶ ተፈራ ደገፌEthiopia Zare (እሁድ የካቲት 29 ቀን 2007 ዓ.ም. March 08, 2015፦) የቀድሞ የኢትዮጵ ብሄራዊ ባንክ ገዢ የነበሩትና፤ በኢትዮጵያ ለባንክ ስራ እድገት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረከቱት፤ አቶ ተፈራ ደግፌ፤ ባለፈው አርብ ማርች 6 ቀን፤ 2015 ዓ.ም. ቫንኩቨር በሚገኝ ሆስፒታል በህክምና ሲረዱ ቆይተው፤ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አቶ ተፈራ ደገፌ በ88 አመታችው አረፉ

Tefera Degefe አቶ ተፈራ ደገፌ"ገንዘቡ በኮሚኒስት ሀገር የሚታተም ከሆነ ስራዬን እለቃለሁ" አቶ ተፈራ ደገፌ ለደርግ ሰዎች

Ethiopia Zare አርብ የካቲት 27 ቀን 2007 ዓ.ም. March 06, 2015፦ የኢትዮጵያ ባንክ ገዥ የነብሩትና ለርዥም ዓመታት ሃገራቸውንና ህዝባቸውን በሙያቸው ያገለገሉት አቶ ተፈራ ደገፌ በቫንኩቨር-ካናዳ በህክምና ሲርዱ ከቆዩ ብኋላ በ88 ዓምታችው ዛሬ አርብ ማርች 6 ቀን 2015 ዓ.ም. ከንጋቱ 11 ሰዓት ተኩልከ (5፡30 am) ማርፋቸው ታወቀ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ናይጄሪያዊቷ ጋዜጠኛ አዴኦላ ፋዩን በአፍሪካ ወቅታዊ ዜናዎች ላይ ተመስርታ በአሸሟሪነት ...

የኢትዮጵያው ባለ475 ሚሊዮን ዶላር ባቡር

"ፍራንስ 24" የተሰኘው የቴሌቭዥን ጣቢያ ዛሬ ዓርብ መጋቢት 4 ቀን ...

ስለሕዳሴው ግድብ የተጠናከረ ዘገባ

ዜና እና ፖለቲካ

ኪነ-ጥበብ

ቪዲዮ

መጻሕፍት

ስለእኛ

ይከተሉን!