Home ዜና Latest መድረክ በአዲስ አበባ ስብሰባ ይጠራል
 
መድረክ በአዲስ አበባ ስብሰባ ይጠራል Print E-mail
Saturday, 26 December 2009 17:50

Ethiopia Zare (ቅዳሜ ታህሳስ 17 ቀን 2002 ዓ.ም. December 26, 2009)፦ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ አንድነት መድረክ መጪውን ምርጫ በማስመልከት ከአዲስ አበባ ነዋሪዎች ጋር ለመወያየት ታህሳስ 25 ቀን ህዝባዊ ስብሰባ ለመጥራት እየተዘጋጀ መሆኑ ታወቀ።

 

የመድረክ ምንጮች እንደገለጹት በመጪው ታህሳስ 25 ቀን 2002 ዓ.ም. ታላቅ ስብሰባ ለማካሄድ በዝግጅት ላይ ሲሆን፣ የስምንት የፖለቲካ ፓርቲዎች ውህድ የሆነው መድረክ ህዝባዊ ስብሰባ ለማካሄድ ለአዲስ አበባ መስተዳደር የፈቃድ ጥያቄ ለማቅረብ በዝግጅት ላይ እንደሚገኝም ለማወቅ ተችሏል።

 

ከምርጫ ቦርድ እውቅና ካገኘ ሁለት ወር እንኳ ያልሞላው መድረክ ከተሳካ ታህሳስ 25 ቀን ከአዲስ አበባ ህዝብ ጋር ለመጀመሪያ ጊዜ የሚወያይ ይሆናል። የመሰብሰቢያ አዳራሹ ስብሰባ ማዕከል ወይም ሜክሲኮ መብራት ኃይል አዳራሻ እንደሚሆንም ምንጮቹ አክለው ገልጸዋል።

 

አዲስ ዜናዎችና ጽሑፎች