| ኢትየጵያዊያን ከ60 ዓመታት በኋላ በሮም ድጋሚ ድል ተቀዳጁ |
|
| Monday, 22 March 2010 10:04 | |
|
Ethiopia Zare (ሰኞ መጋቢት 13 ቀን 2002 ዓ.ም. March 22, 2010)፦ በዓለም ታሪክ ኢትዮጵያን በመወከል በአትሌቲክስ ታሪክ በባዶ እግሩ በመሮጥና በማሸነፍ ተወዳዳሪ ያልተገኘለትን አትሌት አበበ ቢቂላን በመተካት ከአምሳ ዓመታት በኋላ አትሌት ሲራጅ ገና 500 ሜትር ሲቀረው በባዶ እግሩ በመሮጥ አሸነፈ።
በዚሁ በ1952 ዓ.ም. (1960 እ.ኤ.አ.) አበበ ቢቂላ በባዶ እግሩ በመሮጥ የዓለም ክብረ ወሰን ያስመዘገበበት ሮም ከተማ፤ አበበ ቢቂላ ከተወለደበት መንደር የተወለደው ወጣት አትሌት ሲራጅ ገና ለማሸነፍ የቀሩትን 500 ሜትሮች ጫምዎቹን ወርውሮ በማውጣት ታላቁን የሩጫ ሰው ለማሰብ በባዶ እግሩ በመሮጥ ከማሸነፉም በላይ የአበበን ሩጫ በዓይናቸው በማየት በትዝታ ይኖሩ የነበሩ የስፖርቱን አድናቂዎች በድጋሚ በማሳየት ታሪክ መሥራቱን አስመስክሯል።
ትላንት እሁድ መጋቢት 12 ቀን 2002 ዓ.ም. በተካሄደው የሮም ሩጫ ውድድር በሴቶች ከአንድ እስከ ሦስት በመከታተል ኢትዮጵያዊያኖቹ አትሌቶች ፍሬሕይወት ዶባ 2፡25፡28 ሰዓት በማስመዝገብ ውድድሩን ስታጠናቅቅ፤ በመከተልም ከበቡሽ ኃይሌ 2፡25፡31 ሰዓት፤ አትሌት ማሬ ዲባባ ደግሞ በ2፡25፡38 ሰዓት ሦስተኛ ደረጃ በመከታተል ገብተው አሸንፈዋል። |