Home ዜና "ለሁሉም ጊዜ አለው" ዳኛ ወልደሚካኤል መሸሻ
"ለሁሉም ጊዜ አለው" ዳኛ ወልደሚካኤል መሸሻ PDF Print E-mail
Wednesday, 02 April 2008 11:38

Judge Woldemichael MesheshaEthiopia Zare (ረቡዕ መጋቢት 24 ቀን 2000 ዓ.ም. April 2,2008) የኢህአዴግ አገዛዝን በመቃወምና በተለይም ምርጫ 97ን ተከትሎ ሰኔ 1 ቀን 1997 ዓ.ም. እና ጥቅምት 22 ቀን 1998 ዓ.ም. የኢህአዴግ ታጣቂዎች ካደረሱትን ጭፍጫፋ ጋር በተያያዘ ለስደት የተዳረጉት ዳኛ ወልደሚካኤል መሸሻ በኢትዮጵያ ዛሬ ድረ ገጽ ላይ "የፌዴራል ፍርድ ቤቶች አስተዳደር በዳይሬክተሩ ታምሷል" በሚል ርዕስ የወጣውን ዜና ተንተርሰው የግላቸውን ምስክርነት ሰጡ።

 

ዳኛ ወልደሚካኤል መሸሻ የኢትዮጵያ ሚዲያ መድረክ (ኢ.ኤም.ኤፍ.) ድረ ገጽ ላይ "ለሁሉም ጊዜ አለው" በሚል ርዕስ በፃፉት ስድስት ገጽ በፌዴራሉ ፍርድ ቤቶች አስተዳደር ውስጥ ላለው ስር የሰደደ ችግር እማኝነታቸውን ሰጥተዋል። ሙሉውን የምስክክርነት ጽሑፍ ለማንበብ እዚህ ይጫኑ!

 

ዳኛ ወልደሚካኤል ቀደም ሲል የጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኛ፣ በኋላም የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ም/ፕሬዝዳንት የነበሩ ሲሆን፣ የሰኔ አንዱና የጥቅምት 22ቱ አጣሪ ኮሚሽን ምክትል ሰብሳቢ ሆነው ሲሰሩ በተለይ በቀጥታ በጠቅላይ ሚኒስትር መለስ "ሪፖርቱን አስተካክሉ" የሚል ጫና ሲደርስባቸው ትክክለኛውንና ያልተበረዘውን ሪፖርት እንደያዙ ከሀገር መሰደዳቸው አይዘነጋም።

 
 

በጽሑፍ መሳተፍ ለምትፈልጉ በሙሉ!

በማናቸውም ጉዳይ ላይ ያለዎትን ሃሳብ፣ አስተያየት፣ ትችት፣ ግጥም፣ ልብወለድ፣ … በማይክሮሶፍት ወርድ ፕሮግራም በዩኒኮድ ፎንት ጽፈው ከራስዎ ኢ-ሜይል ሳጥን ጽሑፎትን አያይዘው በኢ-ሜይል አድራሻችን ethiopiazare@gmail.com ቢልኩልን ለሥራችን ቅልጥፍና ይረዱናል።

ኢትዮጵያ ዛሬ