Home ዜና የሟቾችን አስከሬን ለማግኘት አራት ቀናት ፈጀ
የሟቾችን አስከሬን ለማግኘት አራት ቀናት ፈጀ PDF Print E-mail
Saturday, 10 May 2008 14:54

Ethiopia Zare (ቅዳሜ ግንቦት 2 ቀን 2000 ዓ.ም. May 10, 2008)፦ እሁድ ሚያዝያ 26 ቀን 2000 ዓ.ም. በድሬዳዋ አካባቢ በጎርፍ አደጋ ከሞቱት አራት ሰዎች ውስጥ የመጨረሻው አስከሬን ኀሙስ ዕለት መገኘቱን ፖሊስ ሀገር ውስጥ ላሉ የመገናኛ ብዙኃን ገለጸ።

 

በድሬዳዋ ከተማ ድል ጮራ ሆስፒታል የሚሠሩ የጤና ባለሞያዎችን ይጓዝ የነበረ መኪና በጎርፍ አደጋ ተጠቅቶ አራቱ መሞታቸውን፣ አንዲት ነርስ መትረፏንና ከሟቾቹ ውስጥ የጤና ባለሙያ የነበረው የአቶ አህመድ ሐሰን አስከሬን ብቻ መገኘቱን ሰኞ ዕለት መዘገባችን አይዘነጋም።

 

ማክሰኞና ረቡዕ በተደረገው የአስከሬን ፍለጋ የጤና ባለሙያ የሆነበረው የጆቫኒ ጥላሁን እና የአርሶ አደር የነበረች ሃፊሻ ሼህ መሐመድ አስከሬን ወደ አምስት ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ተገኝቷል።

 

በመጨረሻም ኀሙስ ዕለት የመጨረሻው አስከሬ ሊገኝ መቻሉን የክልሉ ፖሊስ ገልጿል። አስከሬናቸው መጨረሻ ላይ የተገኘው የመኪናው አሽከርካሪ የነበሩት የአቶ መሐመድ ሰዒድ ነው።

 

የጤና ባለሙያዎቹ በድሬዳዋ ድል ጮራ ሆስፒታል ይሠሩ የነበሩ ሲሆን፣ በገጠር ቀበሌዎች አገልግሎት ሰጥተው እሁድ ዕለት በስምንት ሰዓት ላይ ወደ ድሬዳዋ ለመግባት 17 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው ለገዳኒ በተባለች አካባቢ መኪናቸው በጎርፍ በመጠቃቱ ነው አደጋ የደረሰባቸው። ከተሳፋሪዎቹ ውስጥ የተረፈችው የጤና ባለሙያዋ ፈሪያ አብደላ ብቻ ነበረች።

 
 

መለከት የኢትዮጵያ ራዲዮ በቫንኩቨር - ካናዳ፣ ቅዳሜ July 7, 2008 7 AM - 8 AM (Pacific Time) ስርጭቱን ይጀምራል። በቀጥታ ለማዳመጥ እዚህ ይጫኑ!