|
Tuesday, 23 September 2008 18:18 |
|
ጠ/ሚኒስትር መለስ ይጎበኟታል ተባለ ኢትዮጵያዊያኖች ለተቃውሞ እየተዘጋጁ ነው Ethiopia Zare (ማክሰኞ መስከረም ፲፫ (13) ቀን ፳፻፩ (2001) ዓ.ም. September 23, 2008)፦ ለጉብኝት በሰሜን አሜሪካ ዋና ዋና ከተሞች በመዘዋወር ላይ የምትገኘው ድንቅነሽ (ሉሲ) ከሂውስተን ወደ ሲያትል-ዋሽንግተን የምታቀና ሲሆን፣ ጠ/ሚኒስትር መለስ ጉብኝቱን ትኩረት ለማሰጠት በስፍራው እንደሚገኙ ያወቁ ኢትዮጵያዊያን ለተቃውሞ ከፍተኛ ዝግጅት እያደረጉ መሆኑን የኢትዮጵያ ዛሬ ምንጮች አረጋገጡ።
ጠ/ሚ/ር መለስ በሲያትሉ ካውንስለር አቶ ሠለሞን ታደሰ እና በባለቤታቸው የክብር እንግድነት ግብዣ ተደርጎላቸዋል። ጠ/ሚኒስትሩ ለግብዣው የሰጡት ምላሽ ባይታወቅም ሁኔታውን የሰሙ ኢትዮጵያዊያኖች በመተባበር ከፍተኛ የተቃውሞ እንቅስቃሴ ለማድረግ በዝግጅት ላይ መሆናቸው ታውቋል። ድንቅነሽ በሲያትል ፓሲፊክ ሳይንስ ማዕከል ለአምስት ወራት ለዕይታ ትቀርባለች። |