Home ዜና Latest ከጠ/ሚ/ር መለስ ጋር ኒው ዮርክ የሄደ ጋዜጠኛ ጥገኝነት ጠየቀ
ከጠ/ሚ/ር መለስ ጋር ኒው ዮርክ የሄደ ጋዜጠኛ ጥገኝነት ጠየቀ PDF Print E-mail
Thursday, 02 October 2008 19:59

Ethiopia Zare (ኀሙስ መስከረም ፳፪-22 ቀን ፳፻፩-2001 ዓ.ም. October 2, 2008)፦ ጠ/ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ጋር ወደ ኒው ዮርክ ስብሰባውን ለመዘገብ አብሮ የተጓዘ ካሜራ ቀራጭ ጋዜጠኛ ሸዋንግዛው ካሳሁን ጠ/ሚኒስትሩ ከኮንዶሊዛ ራይዝ ጋር ያደረጉትን የመጨረሻ ስብሰባ ሳይቀርጽ አሜሪካን ሀገር መጥፋቱንና ጥገኝነት መጠየቁ ታወቀ።

 

 

ጋዜጠኛ ሸዋንግዛው በየስብሰባዎቹ የቀረጻቸውን ፊልሞች ባልደረባው ለሆነችው የኢ.ዜ.አ. ጋዜጠኛ ኃይምኖት እንድትይዝለት ከሰጠ በኋላ ጠ/ሚኒስትሩ ከአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኮንደሊዛ ራይዝ ጋር ያደረጉትን ውይይት ይቀርጻል ተብሎ ሲጠበቅ በቦታው አለመገኘቱን ለማወቅ ችለናል።

 

ጋዜጠኛው በአሜሪካ ጥገኝነት እየጠየቀ መሆኑ ሲታወቅ፣ ሌላዋ የኢ.ዜ.አ. ጋዜጠኛ የሆነችው ኃይማኖት አዲስ አበባ መግባቷ ታውቋል።

 

 

ተያያዥ

 
Andenet in Europe, Nov, 2008