ለልጆቹ የእናታቸውን መሞት መንገር እንዳስቸገረው ገለጸ

(ሊመለከቱት የሚገባ ቃለ ምልልስ)

Ethiopia Zare (ማክሰኞ ሚያዚያ 2 ቀን 2004 ዓ.ም. April 10, 2012)፦ በሊባኖስ የኢትዮጵያ ካውንስለር በራፍ ላይ ስትጎተትና ስትሰቃይ የነበረችውና በሊባኖስ ሆስፒታል ህይወቷ ያለፈው ኢትዮጵያዊቷ ወጣት አለም ደቻሳ የሁለት ልጆች አባት የሆነው ለሜሳ ኢጄታ ለልጆቹ የእናታቸውን መሞት ለመንገር እንደተቸገረ እንባ እየተናነቀው ጋርዲያን ለተባለው የዜና አውታር ገለጸ።

 

በብዙ ስቃይ ከቤቷና ከልጆቿ የተለየችው አለም ደቻሳ በሀገር ቤት በነበረች ሰአትም እንጀራ እየጋገረች ቤተሰቦቿን የምታስተዳድር ብርቱ ሴት እንደነበረች የታወቀ ሲሆን ከቤቷ በወታች ጊዜም ከልጆቿ ፈታኝ የሆኑ ጥያቄዎችን ትጠየቅ እንደነበር ለማወቅ ተችሏል።

 

አለም ደቻሳ የ33 አመት እድሜ ያላት ወጣት ስትሆን የአማሟቷ ሁኔታ እንዲጣራ በኢትዮጵያዊያን ዘንድ ከፍተኛ ጉትጎታ እየተደረገ ከመሆኑም በላይ የአለማቀፍ ተቋማት በአለም ደቻሳ ላይ የተፈጸመውን ዘግናኝ ሂደት በትኩረት እየተከታተሉት እንደሚገኝ ተዘግቧል።

 

የአለም ደቻሳ የሁለት ልጆች አባት የሆነው አቶ ለሜሳ ኢጄታ ለጋርዲያን የሰጠውን አሳዛኝ ቃለ ምልልስ ይመልከቱ

አዲስ ቪዲዮ

ዜና እና ፖለቲካ

ኪነ-ጥበብ

ቪዲዮ

መጻሕፍት

ስለእኛ

ይከተሉን!