ዜና - News
የጉጂ እና የቦረና ጎሣዎች ተጋጩ
በግጭቱ ደን ተቃጠለ
Ethiopia Zare (ማክሰኞ የካቲት 25 ቀን 2000 ዓ.ም. March 4,2008)፦ በጉጂ እና በቦረና ጎሣዎች መካከል በተነሳ ከፍተኛ ግጭት በዛሬው ዕለት ደን እንደተቃጠለ ዛሬ ማምሻውን የኢትዮጵያ ዛሬ ምንጮች ጠቆሙ።
ወ/ት ብርቱካን ከደቡብ የም/ቤት አባላት ጋር በአዋሣ ተወያዩ
"የተገነጠሉ አባላት ፓርቲውን አጠናክረው ቢቀጥሉ የሚጠላ ወገን የለም" ወ/ት ብርቱካን
Ethiopia Zare (ማክሰኞ የካቲት 25 ቀን 2000 ዓ.ም. March 4,2008)፦ የቅንጅት ለአንድነትና ለዲሞክራሲ ተቀዳሚ ምክትል ሊቀመንበር ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ በዛሬው ዕለት ወደ አዋሣ ከተማ ተጉዘው በቅንጅት ስም ተመርጠው ደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል ምክር ቤት ከገቡ 23 አባላት ጋር መወያየታቸውን የኢትዮጵያ ዛሬ ምንጮች ገለጹ።
ቅንጅትን በአዲስ ስም ለማስመዝገብ ተወሰነ
Ethiopia Zare (ቅዳሜ የካቲት 22 ቀን 2000 ዓ.ም. March 1,2008)፦ ቅዳሜ ማምሻውን የተሰበሰበው የቅንጅት ለአንድነትና ለዲሞክራሲ ላዕላይ ምክር ቤት ድርጅቱን በአዲስ ስም ለማስመዝገብ የወሰነ ሲሆን፣ በጎደሉ የሥራ አስፈጻሚ ምትክም አምስት አባላትን የመረጠ መሆኑን ከአዲስ አበባ የደረሰን ዘገባ ጠቆመ።
በወ/ት ብርቱካን የሚመራው ላዕላይ ም/ቤት ስበሰባውን ለቅዳሜ አዛወረው
Ethiopia Zare (ዓርብ የካቲት 21 ቀን 2000 ዓ.ም. February 28,2008)፦ በተቀዳሚ ም/ሊቀመንበሯ ወ/ት ብርቱካን የሚመራው የቅንጅት ለአንድነትና ለዲሞክራሲ ፓርቲ ዛሬ ሊያደርገው የነበረውን የላዕላይ ምክር ቤት ስብሰባ ለነገ ቅዳሜ የካቲት 22 ቀን 2000 ዓ.ም. ማዛወሩን ምንጮቻችን ገልፀዋል።
አዲስ አበባ ራጉዔል ቤ/ክ አካባቢ ቦንብ ፈነዳ
በንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ደርሷል
Ethiopia Zare (ዓርብ የካቲት 21 ቀን 2000 ዓ.ም. / February 29,2008)፦ ዛሬ ረፋዱ ላይ በኢትዮጵያ አቆጣጠር ከቀኑ ስምንት ሰዓት አካባቢ መርካቶ በሚገኘው ራጉዔል ቤተክርስቲያን አካባቢ "ቁጭራ" በሚባለው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ አጠገብ ቦንብ ፈንድቶ በንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ያደረሰ ሲሆን፣ ይህንን ዘገባ እስካጠናከርንበት ሰዓት ድረስ በሰው ሕይወት ላይ ያደረሰውን ጉዳት ለማወቅ አልቻልንም።
የእነአቶ ተመስገን ያለመከሰስ መብት እንዲነሳ ተጠየቀ
Ethiopia Zare (ዓርብ የካቲት 21 ቀን 2000 ዓ.ም. February 29,2008)፦ ማህተምና የጽህፈት ቤት መሳሪያዎች አላስረክብም ብለዋልና የነአቶ ተመስገን ዘውዴ ያለመከሰስ የፓርላማ መብት ይነሳልኝና ልክሰሳቸው በማለት አቶ አየለ ጫሚሶ ለፓርላማ ክስ አቀረቡ።
በቂም በቀል ተነሳሰቶ ጎረቤቱን የገደለው ግለሰብ እስካሁን አልተያዘም
• የሟች ቤተሰቦች ስጋት ላይ ወድቀዋል
• አንድ የክልል ባለሥልጣን ለገዳዩ ከለላ ሰጥቶታል ተብሏል
በሸዋዬ ካሳሁን
Ethiopia Zare (አርብ የካቲት 21 ቀን 2000 ዓ.ም. February 29, 2008)፦ ከአዲስ አበባ በስተሰሜን ራያ ቆቦ በተባለው ከተማ በቂም በቀል በመነሳሳት የሰው ሕይወት ያጠፋው ግለሰብ እስካሁን ድረስ በቁጥጥር ሥር ሊውል ባለመቻሉ በየሟች ቤተሰቦች ስጋት ላይ ወድቀዋል።
በአንድ ተማሪ ሞት ዲላ ዩኒቨርስቲ ተረበሸ
Ethiopia Zare (ዓርብ የካቲት 21 ቀን 2000 ዓ.ም. February 29, 2008)፦ ከአዲስ አበባ ከተማ በስተደቡብ በምትገኘው ዲላ ከተማ ባለው «ዲላ ዩኒቨርስቲ» በተገደለ አንድ ተማሪ ምክንያት ዩኒቨርስቲው ተረበሸ። ተማሪውን ገድሎታል በሚል የተጠረጠረው ተማሪም በቁጥጥር ስር ውሏል።
በወ/ት ብርቱካን የሚመራው ላዕላይ ምክር ቤት ነገ አርብ ይሰበሰባል
Ethiopia Zare (ሐሙስ የካቲት 20 ቀን 2000 ዓ.ም. February 28,2008)፦ የቅንጅት ለአንድነትና ለዲሞክራሲ ፓርቲ በተ/ም/ሊ ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ የሚመራው የላዕላይ ምክር ቤት ነገ አርብ ስብሰባ እንደሚያካሂድ ታማኝ ምንጮች ጠቆሙ።
በዶ/ር ታዬ ይመራ የነበረው ኢመማ ለተለጣፊው ተሰጠ
ፍርዱ አግባብ አይደለም ያሉ መምህራን ታፈሱ
‘ውሳኔው ኢ-ፍትሀዊ ነው’ አቶ ገሞራው ካሣ
Ethiopia Zare (ረቡዕ የካቲት 19 ቀን 2000 ዓ.ም. February 27,2008)፦ በ1941 ዓ.ም. የተቋቋመውና ቀደም ሲል በዶ/ር ታዬ ወልደሰማያት ይመራ የነበረው አንጋፋው የመምህራን ማህበር ከ15 ዓመታት የፍርድ ሙግት በኋላ በ1985 ዓ.ም. ለተመሰረተውና በኢህአዴግ ተቀጥላ ለሆነው ቡድን የተወሰነ መሆኑን ከአዲስ አበባ የደረሰን መረጃ ጠቆመ።

