ዘጌርሳም

የረጅም ጊዜ ተንኮላቸው ሳይገባህ

አጀንዳቸውን ሳታነብ ሳይረዳህ

በቋንቋና በባህል አሳበው

መገንጠል አለብህ ብለው አታለው

አንድ ‘ርምጃ ወደፊት አራት ‘ርምጃ ወደኋላ ስበው

የልጆችህን ዕድል አጨልመው

ያንተንም ሕይወት አደንቁረው

የማይገባህን ክቡር ብለው

ከሕዝብ ጋር አጣልተው

የጥላቻ መርዝን ረጭተው

ባልን ከምሽት አለያይተው

ቤተሰባቸውን በትነው

አንተንም አስረውና ገርፈው

ሰብዕናህን አዋርደው

እንደከብት በሜዳ ላይ ነድተው

በእግረ ሙቅ ሲያሰቃዩህ

በጥይት ሲደበድቡህ

ዘቅዝቀው የሉሄ ሲያሰኙህ

ምን ፀፀትና እሮሮ ተሰማህ

አንተማ መስሎህ ነበር

ኢትዮጵያ የምትበተን የምትገነጣጠል

ዓላማህ አንተን የሚያጠፋ ሳይመስልህ

አገር መበታተን እንዲህ ቀላል መስሎህ

ታሪክን በደንብ ባለማንበብህ

ብልሁን የኢትዮጵያን ሕዝብ መበተን

እንደማይቻል ጠላት መረዳቱን

ማውቅና ማጤን ተገቢ ነው

እንኳንስ የዘር ፖለቲካ አራጋቢው

ሌላውም አፍሯል በሙከራው

ኢትዮጵያ ማለት ጠይም ሕዝብ ነው

የሐበሻነት መለያ ያለው

ከሕግ ጋር አብሮ የኖረ

መንግሥት ሳይኖር እራሱን ያስተዳደረ

ተዋልዶና ተካብዶ የሚኖር

ለጠላት ሴራ የማይበገር

ብልህና አስተዋይ ሕዝብ ነው

ሊከበርና ሊደነቅ የሚገባው

አንተማ መስሎህ ነበር

ሕዝብን በማጣላትና በማናቆር

ሥልጣን ከደጅህ ድረስ ሲመጣልህ

ለይስሙላ ፕሬዝደንት ሲሉህ

ልዩ ልዩ ማዕረጎች ሲሾሙህ

ጀኔራል ኮሎኔል ሻለቃ ተብለህ

መትረየስና ክላሽንኮቭ ያለጥይት ተሽክመህ

መልሶ አንተኑ የሚያስመታህ

ከወገንህ አጣልተው

የጥላቻ መርዝ ግተው

የዘርና ጎጥ ኹከት አስነስተው

እንደ ጭቃ ለንቅጠው

እንደ ብረት ቀጥቅጠው

ልክ ሲያስገቡህ ተረዳኸው

አንተማ መስሎህ ነበር

ኢትዮጵያን መበተን ቀላል ነገር

ሲያዘጋጁህ ለእኩይ ተግባር

ማጣፊያ ለሌለው መደናበር

አዲስ ቪዲዮ

ዜና እና ፖለቲካ

ኪነ-ጥበብ

ቪዲዮ

መጻሕፍት

ስለእኛ

ይከተሉን!