ዶ/ር ፍቅሬ ቶለሣ ጂግሳ Dr. Fikre Tolossaዶ/ር ፍቅሬ ቶለሣ ጂግሳ

ይድረስ ለተከበሩ ዶ/ር በያና ሱባ፣ የኦሮሞ ዲሞክራሲ ግንባር አመራር አባል በአሉበት።
ይህን ደብዳቤ እንድጽፍልዎት ያነሳሱኝ ምክንያቶች ርስዎ በቅርቡ ለኢሳት ራዲዮ የሰጡት ቃለመጠይቅ እና አሁን ርስዎ የሚመሩት ከሣምንት በፊት የተቋቋመው "የኦሮሞ ዲሞክራቲክ ግንባር" የወሰዳቸው አቋሞች ናቸው። የርስዎ ቃለመጠይቅና የግንባሩ አዲስ አቋሞች በግሌ እንደአስደሰቱኝ በዚህ አጋጣሚ ልገልጽልዎ እወዳለሁ።

 


ለኔ እንደሚገባኝ፤ አዲሱ ግንባራችሁ የኦሮሞን ህዝብ እና የእናንተንም ጠባብ ምድር ብቻ ሳትሆን መላዋ ኢትዮጵያ መሆኑን ተቀብሎ፤ የኦሮሞን ህዝብ ዕጣ ፈንታ ከመላው የኢትዮጵያ ህዝቦች ጋር አጣምሮ ለመታገል አብስሯል። ይህም አቋም ለኦሮሞ ህዝብ ታላቅ የፖለቲካ እመርታ ነው። የኦሮሞ ነፃነት ግንባር ከጥንቱ፣ ከጠዋቱ፣ ከጥንስሱ ይህን ጥርት ያለ አቋም ይዞ ቢሆን ኖሮ ምናልባት ዛሬ ኢትዮጵያን የሚመራት እሱ በሆነ ነበር። የመላውን የኢትዮጵያ ህዝቦች ድጋፍና ትብብር ያገኝ ነበርና። ከዚህም በላይ ያ ሁሉ ደም ላይፈስ፣ ያ ሁሉ ሰው ላይፈናቀል፣ ላይሰደድና ለእስር ላይዳረግ በቻለ ነበር።


ርግጥ ለኦሮሞ ዝርያዎች በግለሰብ ደረጃም ሆነ አልሆነ ኢትዮጵያን መምራትና ማስተዳደር አዲስ ክስተት አይደለም። ከዛሬ 3500 ዓመታት ጀምሮ ይህን ሲያደርጉ ኖረዋል። ከዛሬ ሁለት ሺ ዓመታት በፊት በአመራር ላይ ከነበሩ ኦሮሞዎች መሃል አንዲት ሴት እና ወንድ ለመጥቀስ ያህል በመርዌ የነገሠችው የሕንደኬዋ ንግሥት፣ የመደባይዋ ጎሣ ሢያኖን በአፄ ፈንታሌ ጊዜ ከፍተኛ ሥልጣን የነበራትና የጂማውን ንጉሥ መጋልን እንዘክራለን። ይህም የጂማ ትልቅ ንጉሥ፣ የመደባይን ካህናት ይዞ፣ በአፋር መርከብ ተሳፍሮ ፖርቱጋልን እና ስፔይንን ለአጭር ጊዜ ከመያዙም በላይ እየሱስ ክርስቶስ በተወለደ ጊዜ ከአስራ አንድ የኢትዮጵያ ዝርያዎች ነገሥታት ወ ጠቢባን ወንድሞቹ ጋር ሆኖ፣ ኢትዮጵያ ግዛት ላይ የታየችውን ኮከብ ተከትሎ ወደ ቤተልሔም ተጉዞ ለዓለሙ ሁሉ ፈጣሪ ለእየሱስ ክርስቶስ ጋዳ እንዳበረከተ ታሪክ ዘግቧል።
... ሙሉውን የዶ/ር ፍቅሬን ጽሑፍ በፒ.ዲ.ኤፍ. ለማንበብ እዚህ ይጫኑ! 

አዲስ ቪዲዮ

ዜና እና ፖለቲካ

ኪነ-ጥበብ

ቪዲዮ

መጻሕፍት

ስለእኛ

ይከተሉን!