“ዶ/ር ብርሃኑ ያቋቋመውን ንቅናቄ አልተቀላቀልኩም። የሚወራው ሁሉ ሐሰት ነው” ዶ/ር አድማሱ ገበየሁ
የቅንጅት ለአንድነትና ለዴሞክራሲ የቀድሞ ም/ሊቀመንበርና፤ ቅንጅት አዲስ አበባን ተረክቦ ቢሆን ኖሮ ለአዲስ አበባ በምክትል ከንቲባነት ተመርጦ የነበረው ዶ/ር አድማሱ ገበየሁ በተለይ በሀገር ውስጥ ባሉ አንዳንድ የመገናኛ ብዙኀን ግንቦት 7 ንቅናቄን እንደተቀላቀለ ተደርጎ የሚናፈሰውን ወሬ አስመልክቶ በሀገር ውስጥ የሚታተመው የእንቢልታ ጋዜጣ ቃለምልልስ አድርጎለታል።
በዚሁ ቃለምልልስ ላይ ዶ/ር አድማሱ ከቀረቡለት ጥያቄዎች ውስጥ የሚከተሉት ይገኙበታል። ከአንድነት ፓርቲ ጋር ያለውን ግንኙነት፣ ከዶ/ር ብርሃኑ ጋር ሎንዶን ላይ እሁድ ሰኔ 1 ቀን 2000 ዓ.ም. (June 8, 2008) ስላደረጉት ህዝባዊ ውይይት፣ በሠላማዊ ትግል ላይ ያለውን አቋም፣ በፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል ስላለው የእርስ በእርስ መጠላለፍ፣ በቀድሞው ቅንጅት ውስጥ ስለተከሰተው መከፋፈል፣ በአመራሮቹ ውስጥ የሥልጣን ሽኩቻ ስለመኖር አለመኖሩ፣ እንዲሁም ሌሎች ተያያዥ ጥያቄዎች ቀርበውለት ምላሽ ሰጥቶባቸዋል። ሙሉውን የእንቢልታ ቅጽ አንድ፣ ቁጥር 27 ዕትምን ቃለምልልስ ለማንበብ እዚህ ይጫኑ!