በጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ሪፖርት ላይ የተደረገ ውይይት
ጠ/ሚ ኃይለማርያም ደሳለኝ ባለፈው ሐሙስ መጋቢት 1 ቀን 2008 (ማርች 10፣ 2016 እ.ኤ.አ.) ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የ6 ወራት የአፈፃም ሪፖርት ሲያቀርቡ፤ በኦሮሚያ ክልል እና በሌሎችም ክልሎች ለተፈጠሩት ችግሮች ፓርቲዬ ኃላፊ ነው ሲሉ ተደምጠዋል።
የቪኦኤው ጋዜጠኛ አዲሱ አበበ የቀድሞውን የህወሓት የማዕከላዊ ኮሚቴ አባልና የአሁኑን የዓረና ፓርቲና የመድረክ አመራር አባል የሆኑት አቶ ገብሩ አስራትን፣ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የታሪክና የሥነጥበብ መምህር የሆኑትን አቶ አበባው አያሌውን፣ እንዲሁም ፕ/ር አለማየሁ ገብረማርያም በካሊፎርኒያ ስቴትስ የፖለቲካ ሣይንስ እና የሕገመንግሥት ጉዳዮች መምህርን አወያይቷል። ውይይቱን ለማድመጥ የማጫወቻ ቁልፉን ይጫኑ!