“በብሔረሰብ ከመደራጀት መላቀቅና ርዕዮተዓለማዊ ፍልስፍና ላይ በተመሠረተ ዕይታ መደራጀት አለብን” ዶ/ር ፈቃዱ በቀለ
”ቅኝ ገዥዎች ለመስፋፋት ሲሉ የብሔር ክፍፍልን በመጠቀም አገሮች እንዳይዳብሩ ያደርጉ ነበር። በእኛም አገር በማወቅም ይሁን ባለማወቅ ብሔር ተኮር የፖለቲካ ኃይሎች ለውጥ ለማምጣት ቢሞከርም፤ ላለፉት ሃምሳ ዓመታት ይህ አልሠራም። ከብሔር ተኮር ይልቅ የአገሪቱ መሠረታዊ ችግሮች የእድገት፣ የሥልጣኔ፣ የሣይንስና ቴኮኖሎጂ፣ የማኅበራዊ ናቸውና ብሎ ቢንቀሳቀስ ኑሮ፤ ዛሬ የምናየው እጅግ አደገኛ ሁኔታ ላይ ባልወደቅን ነበር። በእነዚህ ላይ ቢተኮር ኑሮ እስካሁን ለውጥ ይመጣ ነበር።” ይላሉ ዶ/ር ፈቃዱ በቀለ ከኤስ.ቢ.ኤስ. ጋር ባደረጉት ቆይታ።
ዶ/ር ፈቃዱ በቀለ ቀደም ሲል የነበራቸውንና አሁን ያላቸውን ምሁራዊ አመለካከት ጨምሮ፤ የኢትዮጵያ የፖለቲካ ኃይሎች በየትኛ መስመር ቢጓዙ መሠረታዊ ለውጥ ለአገሪቱም ሆነ ለሕዝብ ሊያመጡ እንደሚችሉ ምሁራዊ አስተያየታቸውን በዚህ ቃለምልልስ ለግሰዋል። ዶ/ር ፈቃዱ ከኤስ.ቢ.ኤስ. ጋር ያደረጉትን ሙሉውን ቆይታ ለማድመጥ የማጫወቻ ቁልፉን ይጫኑ!