ጋዜጠኛ ዳዊት ከበደ ከሲኤንኤን ጋር

Star InactiveStar InactiveStar InactiveStar InactiveStar Inactive

Ethiopia Zare (ረቡዕ ግንቦት 17 ቀን 2003 ዓ.ም. May 25, 2011) ፦ የሲፒጄን “የዓለም አቀፍ ፕሬስ ነፃነት ሽልማት” አሸናፊ የሆነውን ጋዜጠኛ ዳዊት ከበደን ሲኤንኤን “አፍሪካን ቮይስስ” በተሰኘው ፕሮግራሙ ላይ ቃለምልልስ አድርጎለታል። ፕሮግራሙ የተላለፈው ማክሰኞ ግንቦት 16 ቀን 2003 ዓ.ም. (ሜይ 24 ቀን 2011 እ.ኤ.አ.) ሲሆን፤ በዚህ ቃለምልልስ ጋዜጠኛ ዳዊት ስለራሱ፣ ጋዜጠኝነት በኢትዮጵያ ውስጥ ምን እንደሚመስል፣ ተመዘገበ ስለተባለው የኢኮኖሚ ዕድገት፣ … በአጠቃላይ በሀገሪቱ ያለውን ተጨባጭ ሁኔታ ሰፋ አድርጎ አብራርቷል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

”ወለላዬ ከስዊድን” ማን ነው?

Star InactiveStar InactiveStar InactiveStar InactiveStar Inactive

የኢትዮጵያ ዛሬ እድምተኛ ከሆኑ ”ወለላዬ” የሚለውን የገጣሚ የብዕር ስም ያውቁታል። የብዕር ስሙ ባለቤት ነዋሪነቱ ስዊድን ለመሆኑም ”ወለላዬ ከስዊድን” በመሆኑ ይጠፋዎታል ብለን አንገምትም። በተለይም ኢትዮጵያ ዛሬን ሁሌም ሲከፍቱ ”የረቡዕ ግጥም”ን በቀኝ በኩል ማንበብዎ አያጠራጥርም። ”ወለላዬ” ማን ነው? ”የረቡዕ ግጥም” ለምን ተባለ? አጫጭር ግጥሞችን ለምን መረጠ? ”ወለላዬ” የሚለውን የብዕር ስም ለምን መረጠ? ወደ ገጣሚነት እንዴት ገባ? ... ሌሎችንም ጥያቄዎች አስመልክቶ የጀርመን ድምፅ ራዲዮው ጋዜጠኛ ተክሌ የኋላ ከወለላዬ ጋር ያደረገውን ቃለምልልስ አቅርበንልዎታል። (ለማዳመጥ የማጫወቻ ቁልፉን ይጫኑ!)

አርቲስት አብራር አብዶና ደበበ እሸቱ ስለዶ/ር ጥላሁን ገሠሠ ምን ብለው ነበር

የአንባብያን ድምፅ: 2 / 5

Star ActiveStar ActiveStar InactiveStar InactiveStar Inactive

ሊመለከቱት የሚገባ!

Ethiopia Zare(ዓርብ ግንቦት 12 ቀን 2003 ዓ.ም. May 20, 2011) ፦ ሁለቱን ታዋቂ አርቲስቶች አብራር አብዶን እና ደበበ እሸቱን ጨምሮ ሌሎችም ስለየሙዚቃው ንጉሥ ዶ/ር ጥላሁን ገሠሠ የተናገሩትን ፋሲል በቀለ ከስዊድን በድምፅና በምስል በሁለት ክፍሎች በመክፈል እንደሚከተለው አጠናክሮታል። (ለመመልከት የማጫወቻ ቁልፉን ይጫኑ! ሁለተኛውን ክፍል ለመመልከት ደግሞ ከቪዲዮው በታች ያለውን ”ሙሉውን አስነብበኝ ...” የሚለውን ይጫኑ!)

ክፍል ፩

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

“ቤን አሊን ተመልከቱ፣ ሙባረክን ወይንም ጋዳፊን ስሟቸው ሁሉም ህዝባዊ ጥያቄ ሲበረታባቸው የሰጡት መልስ ተመሳሳይ ነው። ‘እኔ ስልጣኔን ብልቅ ሀገሪቱ ቀውስ ውስጥ ትገባለች የእርስ በርስ ጦርነትም ይከሰታል።’ ነበር ያሉት ይህ የተበላበት ክርክር ሲሆን የሚያሳዝነው ግን የምእራቡ አለም መሪዎች በተወሰነ ደረጃ ሊቀበሉት የመፈለግ አዝማሚያ የሚያሳዩ መሆናቸው ነው። “ይህ ወቅት በተግባር ያረጋገጠው ነገር ሌላው ቀርቶ የተቃዋሚ ፓርቲ ሳይኖር እንኳን ህዝብ ነጻነቱን ካገኘ ወደ እርስ በርስ ጦርነት የማያመራ መሆኑን ነው። ህዝቡ ነጻነት የሚመጣው ከሀላፊነት ጋር መሆኑን ጠንቅቆ ይገነዘባል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ መጽሐፉን አስመልክቶ ከተስፋዬ ገብረአብ ጋር የተደረገ ቃለምልልስ

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

Yederasiw Mastawesha / የደራሲው ማስታወሻደራሲና ጋዜጠኛ ተስፋዬ ገብረአብ (ከነፃነት አሳታሚ ኤጀንሲ)

“በአዲሱ መጽሐፍ ቀደም ሲል ልገልፃቸው ያልፈለግሁትን ጭምር ይፋ አድርጌያለሁ” ጋዜጠኛና ደራሲ ተስፋዬ ገብረአብ

የኢትዮጵያውያን ባለአክስዮኖች ንብረት የሆነው “ነፃነት የመጻሕፍት አሳታሚና አከፋፋይ” በቅርቡ፣ “የደራሲው ማስታወሻ” የተባለውን መጽሐፍ አሳትሟል። መጽሐፉ አፕሪል 10 ቀን 2010 እ.ኤ.አ. ለህዝብ ይቀርባል ተብሎ እየተጠበቀ ነው። አሳታሚው ከመጽሐፉ ደራሲ ከተስፋዬ ገብረአብ ጋር በመጽሐፉ ዙሪያ አጭር ቃለመጠይቅ አካሂዷል። የመጽሐፉ አንባብያን ስለመጽሐፉ ይዘት ግንዛቤ ይኖራቸው ዘንድ የቃለመጠይቁን ጭማቂ በዚህ መንገድ ቀርቧል። ሙሉውን አስነብበኝ ...

"በጣም በጥሩ ጤንነት ላይ እገኛለሁ፤ ጥሩ የመንፈሥ መነቃቃት አለኝ" ቴዲ አፍሮ

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

Teddy Afro, ቴዲ አፍሮ ”ግዕዝ ብማር ደስ ይለኛል”

ወጣቱ፣ እውቁና ታዋቂው ድምፃዊ ቴዲ አፍሮ ከእስር ከተለቀቀ ሦስት ወር የሆነው ሲሆን፣ በውጭ ሀገር ከሚገኙ ኢትዮጵያውያን የመገናኛ ብዙኀን ጋር ሰፋ ያለ ቃለምልልስ ያደረገው ከኢትዮጵያ ዛሬ ድረገጽ ጋር ሲሆን፤ ቃለምልልሱን ያደረገው ከኢትዮጵያ ዛሬ ድረገጽ አዘጋጅ ጋዜጠኛ ያሬድ ክንፈ ጋር ነው። በዚህ ቃለምልልስ ላይ ያሬድ በቴዲ አፍሮ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ፣ በቴዲ እስር ቤት ቆይታ ላይ፣ በድምፃዊው የሙዚቃ፣ የግጥምና የመድረክ ሥራ ላይ፣ በአርቲስቱ የግል ሕይወት ጉዳይ ላይ፣ ባለፈው ጥቅምት 1 ቀን 2002 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ስታዲየም ለምን ”ያስተሰርያል” የሚለውን ዘፈን እንዳልዘፈነ፣ በስዊድንና በኖርዌይ ኮንሰርቶቹ እሰጥ አገባና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ የሚያተኩሩ ጥያቄዎችን ለአርቲስት ቴዲ አፍሮ አቀርቦለታል። አርቲስት ቴዲ አፍሮን ለቃለምልልሱ እያመሰገንን፤ መልካም ንባብ ለአንባቢዎቻችን እንመኛለን!

ሙሉውን አስነብበኝ ...

“ኢህአዴግ መስቀለኛ መንገድ ላይ የቆመ ፓርቲ ነው” አቶ ስየ አብርሃ (ቃለምልልስ)

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active
  • ስለወ/ት ብርቱካንና ስለሌሎች ወገኖቻችን መታሰር ከኢህአዴግ እና ከመንግሥት ጋራ በሚደረግ ድርድር ጉዳዩ መነሣት ይገባዋል
  • በመከላከያ፣ በደኅንነት ፖሊሲዎች እና በተቋማት ግንባታ ዙሪያ የማማከር አገልግሎት ለመስጠት ሥራ ጀምሬያለኹ
  • ኢህአዴግ ነፃነትና ነፃ ምርጫን እንደ ጦር የሚፈራበት ደረጃ ላይ ደርሷል
  • ለኢሠፓ እና ደርግ የበለጠ የሚቀርበው ኢህአዴግ እንጂ ተቃዋሚዎች አይደሉም
  • የኢህአዴግ አመራር ለ30 እና ለ40 ዓመታት በሥልጣን ላይ ለመቆየት ቆርጧል
  • የግል ኑሮዬ በፖለቲካ ጥገኛ እንዲኾን አልፈልግም
  • መጽሐፍ ጽፌያለኹ፤ አቅሙ ከተገኘ በቅርብ ይወጣል

አቶ ስየ አብርሃ (የቀድሞ የመከላከያ ሚንስቴር ሚንስትር)

በሐምሌ ወር 1999 ዓ.ም. ከእስር ከተፈቱ በኋላ አንድ አገራዊ ፕሮጀክት ይዘው እየሠሩ ይገኛሉ። ከቀድሞው የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ፕሬዝዳንት ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ጋራ ስምንት የፖለቲካ ፓርቲዎችን በማቀናጀት “የኢትዮጵያ ፌደራላዊ አንድነት መድረክ” በተሰኘው ጥምረት ምሥረታ ግንባር ቀደም ተዋናይ ናቸው። እርሳቸው “የጠንካራ ተቃዋሚን ክፍተት የሚሞላ ትልቅ አገራዊ ፕሮጀክት ነው” ይሉታል - ጥምረቱን። ለአንድ ዓመት ከስድስት ወር በምክክር የቆየውን መድረከ ለጥምረት ካደረሱት እና በጥምረቱ ብሥራት ወቅት በታዛቢነት ከተሳተፉት የቀድሞው የመከላከያ ሚኒስተር ሚኒስትር አቶ ስየ አብርሃ ጋራ የአዲስ አድማስ ጋዜጠኛ ጽዮን ግርማ ሰፋ ያለ ቃለምልልስ አድርጋለች። ቃለምልልሱን እነሆ! መልካም ንባብ!

ሙሉውን አስነብበኝ ...

“ህዝቡ ያሳየኝን ፍቅር ከፍዬ አልጨርሰውም” ቴዲ አፍሮ

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

Exclusive Interview by Tsion Girma

Big mother kiss ከእናቱ ጋራ ሻማ ሊያበራ
 

ከአንድ ዓመት ከአራት ወር እስር በኋላ የተለቀቀው ድምፃዊ ቴዲ አፍሮ የመጀመሪያውን ሰፋ ያለ ቃለምልልስ ከጋዜጠኛ ጽዮን ግርማ ጋር አድርጓል። ቃለምልልሱ የእስር ቤት ቆይታው ምን ይመስል እንደነበር፣ ጊዜውንስን በምን ሁኔታ ያሳልፍ እንደነበር፣ ምን እንዳጋጠመው፣ አብረውት ታስረው ስለነበሩት እስረኞች፣ ከእስር ነፃ ከሆነ በኋላ የሚኖረውን የሙዚቃ ሕይወት፣ ስለወላጅ እናቱ፣ በፍርዱ ላይ የተሰማውን ስሜት፣ ስለአድናቂዎቹ፣ ስለጠያቂዎቹ፣ ስለግጥሞቹ፣ ስለዶ/ር አርቲስት ጥላሁን ገሠሠ፣ … በአጠቃላይ ስለባለፉት 484 ቀናት እና ስለወደፊት ዕቅዱ ያስዳስሰናል። መልካም ንባብ! ሙሉውን አስነብበኝ ...