“ህወሓት ፀረ-ኢትዮጵያ ድርጅት ነው፤ መለስ ኢትዮጵያዊ አይደለም” አብርሃ በላይ (የኢትዮ-ሚዲያ ዋና አዘጋጅ)

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

ከኢካድ ፎረም ተክለሚካኤል አበበ የኢትዮ-ሚዲያ ድረ ገጽ ዋና አዘጋጅ ከሆነው ጋዜጠኛ አብርሃ በላይ ጋር ቃለምልልስ አድርጓል። ቃለምልልሱ በተለይም በአቶ ስዬ አብርሃ፣ በህወሓት እና በትግራይ ህዝብ ጉዳይ ዙሪያ ያተኮረ ነው። ጋዜጠኛ አብርሃ በአሁን ሰዓት የትግራይ ህዝብ ህወሓትን እንደማይወደው በቃለምልልሱ ላይ የገለጸ ሲሆን፣ ከፓርቲው ጋር እየሠሩ ያሉትን ሆነ ሲሰሩ የቆዩት ሰዎች “ፀረ-ኢትዮጵያዊ” መሆናቸውንና ፓርቲውም ፀረ-ኢትዮጵያዊ ድርጅት ነው ሲል ገልጿል። ጠ/ሚ መለስ፤ "ኢትዮጵያዊ አይደለም" ይላል ጋዜጠኛ አብርሃ በቃለምልልሱ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

“በኢትዮጵያ በፈቃድ ሥልጣን የመልቀቅ ባህልን መስበር እፈልጋለሁ” ጠ/ሚ መለስ

የአንባብያን ድምፅ: 4 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Inactive

PM Meles Zenawi ጠ/ሚር መለስ ዜናዊጠ/ሚር መለስ ዜናዊ ከእንግሊዙ “ፋይናንሽያል ታይምስ” ጋዜጣ (የጁን 23, 2009 ዕትም) የአፍሪካ ዴስክ አዘጋጅ ዊልያም ዋሊስ ጋር በጽሕፈት ቤታቸው ባደረጉት ቃለምልልስ፤ በኢትዮጵያ በፈቃድ ሥልጣን የመልቀቅ ባህልን መስበር እንደሚፈልጉና የመጀመሪያው በፈቃደኝነት ሥልጣኑን ለቀቀ የሀገሪቱ መሪ ለመሆን እንዳቀዱ ገልፀዋል። በርካታ ኢትዮጵያውያን የጠ/ሚ/ሩን አባባል በጥርጣሬ ከመመልከታቸውም ባሻገር “ሐሰት ነው” የሚል እምነት እንዳላቸው ይታመናል። ይኸው ቃለምልልስ ከግንቦት 7 ጋር በተያያዘ ስለታሰሩት፣ በፀረ-ሽብር ረቂቅ ሕጉ፣ በሀገሪቱ ኢኮኖሚ፣ ፖለቲካ፣ ... ጉዳዮች ላይ አተኩሯል። ቃለምልልሱን በሀገር ውስጥ የሚታተመው “ሪፖርተር” ጋዜጣ እንደሚከተለው ወደ አማርኛ ተርጉሞታል። መልካም ንባብ!

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ፕ/ት ኢሣያስ አፈወርቂ ከስዊድን ቴሌቭዥን ጋር ያደረጉት ቃለምልልስ (ቪዲዮ)

የአንባብያን ድምፅ: 4 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Inactive

ፕ/ት ኢሣያስ አፈወርቂ በተለይ ለስዊድን ቴቬፊራ (ቲቪ4) ከጋዜጠኛ ዶናልድ ቡስትረም ጋር በእንግሊዝኛ ያደረጉትንና የሰባ ደቂቃ ቃለምልልስ ከዚህ በታች ባለው ቪዲዮ ላይ የማጫወቻ ቁልፉን በመጫን ማየትና ማድመጥ ይችላሉ። ሜይ 26 ቀን 2009 እ.ኤ.አ. የተላለፈ።

 

 

 

ከወ/ት ብርቱካን ወላጅ እናትና ከልጇ ህጻን ሐሌ ጋር የተደረገ ቃለምልልስ

Star InactiveStar InactiveStar InactiveStar InactiveStar Inactive

Hale Mideksa, W/t Birtukan's daughterW/o Almaz G.Egziabeher, W/t Birtukan's mother"እናቴ ናት፣ እወዳታለሁ! ስሄድ እቅፍ አደርግና እስማታለሁ፤ እሷም ትወደኛለች" ህጻን ሐሌ

"ለእኔ ከላይ ከታች ያለችኝ፣ ጧሪ ቀባሪዬ እሷው ናት" ወ/ሮ አልማዝ

የአንድት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ሊቀመንበር ብርቱካን ሚደቅሳ ወላጅ እናት የ72 ዓመቷ ወ/ሮ አልማዝ ገ/እግዚያብሔር በእስር ላይ ስለምትገኘው ልጃቸው እንዲሁም የአራት ዓመት ልጇ ሐሌ ሚደቅሳ ከአዲስ አድማስ ዘጋቢ ጋር ያደረጉትን ቆይታ እንደሚከተለው እናቀርበዋለን።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ፕ/ር መስፍን መደብደባቸውንና የወ/ት ብርቱካንን መታሰር አስመልክቶ ከቪኦኤ ጋር ያደረጉት ቃለምልልስ

Star InactiveStar InactiveStar InactiveStar InactiveStar Inactive

የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ሊቀመንበር የሆኑትን ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳን መታሰርና የፕ/ር መስፍን ወልደማርያምን በደህንነቶች መደብደብን አስመልክቶ የአሜሪካ ድምፅ ራዲዮ ፕሮፌሠር መስፍን ወልደማርያምን ቃለምልልስ አድርጎላቸው ነበር። ቃለምልልሱን አቶ ግርማ ካሳ እንደሚከተለው በጽሑፍ አቀናብሮታል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

”ሀገሬን ትቼ አልቀርም” ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ

Star InactiveStar InactiveStar InactiveStar InactiveStar Inactive

W/t Birtukan Mideksa“ኢትዮጵያን ሪቪው የተባለው ድረ-ገጽ ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ አውሮፓ እንደሚቀሩ መዘገቡን ተከትሎ ሀገር ቤት ያሉ ጋዜጦችም ይህንኑ ማውጣታቸውን ሰማሁና ወዳሉበት ጀርመን ሀገር ስልክ ደውዬ አገኘኋቸው፤ ለጥያቄዎቼም ምላሽ ሰጥተውናል” የሚለን ያሬድ ክንፈ ከስዊድን ነው። ሙሉውን አስነብበኝ ...

”የኔ አጋርነት በኢትዮጵያ ውስጥ ለዲሞክራሲ ሥርዓት ከሚታገሉ ኃይሎች ጋር ነው” አና ጐሜዝ

የአንባብያን ድምፅ: 4 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Inactive

 'ለተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎች ጥሪ የማቀርበው ነገር፤ ህዝቡ በምርጫ እንዳይሳተፍ የሚከለክል መልዕክት ማስተላለፍ አይገባቸውም'

 

Ana Gomesበአውሮፓ ፓርላማ የሶሻሊስት ፓርቲ አባልና በኢትዮጵያ ግንቦት 7 ቀን 1997 ዓ.ም. ተካኺዶ በነበረው ምርጫ የአውሮፓ ምርጫ ታዛቢ ልዑካን ሊቀመንበር የነበሩት አና ጐሜዝ በቅርቡ ከዩሮ ጋዜጣ ጋር በኢትዮጵያ ስላለው የዲሞክራሲ ሁኔታ፣ ስለኦነግ (ስለየኦሮሞ ነፃነት ግንባር)፣ በቀጠናው ስላለው መረጋጋትና ”የቅርብ ወዳጃቸው ናቸው” ተብለው ስለሚጠቀሱት በዶ/ር ብርሀኑ ነጋ ስለተቋቋመው የግንቦት 7 ንቅናቄ ዙሪያ ያደረጉትን ቃለ-ምልልስ ለኢትዮጵያውያን አንባብያን በሚመች መልኩ በአማርኛ ቋንቋ ተርጉመን አቅርበነዋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የአሜሪካ ምርጫ በኢትዮጵያ ተቃዋሚዎች ዕይታ

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

Bulcha Demeksa
አቶ ቡልቻ
”… በሰው ሀገር ምርጫ ማንስ ቢመረጥ እኔ ምን አገባኝ? ከዚህ በፊት ሌሎች ጋዜጦች ጠይቀውኝ አስተያየት የለኝም ብያለሁ …” ሲሉ የኦፌዲን ሊቀመንበር አቶ ቡልቻ ደመቅሳ፤ ዓለም ጆሮውን ተክሎ የሚከታተለውን፣ የአሜሪካ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ አስመልክቶ ማን እንዲመረጥ ይፈልጋሉ? በሚል እንቢልታ ጋዜጣ ላቀረበላቸው ጥያቄ ምላሽ ሰጥተዋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...