ጋዜጠኛ መአዛ ብሩ ከጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ ጋር ያደረገችው ቃለምልልስ (ክፍል ፩)
በኢትዮጵያ ውስጥ አንድ በሥልጣን ላይ ያለ ጠቅላይ ሚንስትር ለግል ሚድያ ሰፊ ቃለምልልስ ሰጥቶ አያውቅም። ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ለመጀመርያ ጊዜ ሰፊ ቃለምልልስ ለመሥጠት በቅተዋል፤ ቃለመጥይቁን ያደረገችው ደግሞ በሸገር ኤፍ.ኤም. በጨዋታ እንግዳ ፕሮግራም ላይ ጋዜጠኛ መአዛ ብሩ ነች።
ዝግጅቱ የተላለፈው ዛሬ ቅዳሜ መስከረም ፫ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. (September 14, 2019) ነው። ቃለምልልሱን ለማድመጥ የማጫወቻ ቁልፉን ይጫኑ!