Logo

በኮቪድ 19 (ኮሮና ቫይረስ) የተነሳ የሟቾች ቁጥር በኢትዮጵያ እየጨመር ነው

በኮቪድ 19 (ኮሮና ቫይረስ) የተነሳ የሟቾች ቁጥር በኢትዮጵያ እየጨመር ነው

በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር 32 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል

ኢዛ (ሰኞ መጋቢት ፮ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. March 15, 2021)፦ በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ በማኅበረሰቡ ውስጥ በከፍተኛ የመባዛት ደረጃ ላይ እንደሚገኝ እና በቫይረሱ ተይዘው የሚሞቱ ሰዎች 89 በመቶ ጭማሪ ማሳየቱን የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዛሬ ሰኞ መጋቢት 6 ቀን 2013 ዓ.ም. ባወጣው መግለጫ አስታወቀ።

ባለፉት ሰባት ቀናት 49 ሺህ 326 ሰዎች ተመርምረው 9 ሺህ 329 ግለሰቦች ቫይረሱ እንደተገኘባቸው እና ይህም ከ100 ግለሰቦች በአማካኝ 19 በመቶ ሰዎች ቫይረሱ እንደተገኘባቸው ያመለክታል ብሏል።

ካለፉት ሳምንታት ጋር ሲነጻጸር በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር 32 በመቶ መጨመሩን ያመላከተው ኢንስቲትዩቱ፤ በቫይረሱ ተይዘው የሚሞቱ ሰዎች ቁጥርም እየጨመረ ነው። በአንድ ሳምንት ውስጥ 121 ግለሰቦች ሕይወታቸውን ሲያጡ፤ ካለፉት ሳምንታት አንጻር 89 በመቶ ጭማሪ ማሳየቱንም አስታውቋል።

በወረርሽኙ ተይዘው ወደ ጽኑ ሕሙማን ሕክምና ክፍል የሚገቡ ግለሰቦች ቁጥርም ከዕለት ወደ ዕለት እየጨመረ ሲሆን፤ ትናንት ብቻ 467 ሰው በጽኑ ሕሙማን ክፍል ውስጥ ይገኛሉ ብላል። (ኢዛ)

© ፳፻ - ፳፻፲፬ ዓ.ም. ኢትዮጵያ ዛሬ፣ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው። Copyright © 2007 - 2022 Ethiopia Zare. All Rights Reserved.