Logo

Former Nigerian President Olusegun Obasanjo

የቀድሞው የናይጄሪያ ፕሬዝዳንት ኦሊሴጎን ኦባሳንጆ

ኦሊሴጎን ኦባሳንጆ በአፍሪካ ሕብረት የምርጫ ታዛቢ ቡድን ኃላፊ ናቸው

ኢዛ (ዓርብ ሰኔ ፲፩ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. June 18, 2021)፦ ከአንድ መቶ በላይ ታዛቢዎች ይገኙበታል ተብሎ የሚጠበቀው ስድስተኛ አገራዊ ምርጫ 2013ን ለመታዘብ ታዛቢዎች ወደ ኢትዮጵያ እየገቡ ነው።

በትናንትናው ዕለትም በአፍሪካ ሕብረት የምርጫ ታዛቢ ቡድን ኃላፊ የኾኑት የቀድሞው የናይጄሪያ ፕሬዝዳንት ኦሊሴጎን ኦባሳንጆ ማምሻውን አዲስ አበባ ገብተዋል።

የ84 ዓመቱ ኦሊሴጎን ለስምንት ዓመታት የናይጄሪያ ፕሬዝዳንት ኾነው አገሪቱን የመሩት እ.ኤ.አ ከ1999 እስከ 2007 እንደነበር ይታወሳል። (ኢዛ)

© ፳፻ - ፳፻፲፬ ዓ.ም. ኢትዮጵያ ዛሬ፣ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው። Copyright © 2007 - 2022 Ethiopia Zare. All Rights Reserved.