Amhara region

የአማራ ክልል

“አሁን ያለው ሁኔታ ለክልሉም ኾነ ለመላው አገሪቱ የፀጥታ ስጋት ወደመኾን ተሸጋግሯል” የደኅንነትና የፀጥታ ካውንስሉ

ኢዛ (ሐሙስ ጥቅምት ፮ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. October 17, 2019):- ካለፉት አምስት ዓመታት ወዲህ በቅማንት ብሔረሰብ ማንነት ጥያቄና በተያያዙ ምክንያቶች የሚታየውን የፀጥታ መደፍረስ ለማረጋጋት፤ የፌዴራል መንግሥት ጣልቃ እንዲገባ መወሰኑንና በአካባቢው ያለውን የፀጥታ ችግር አስመልክቶ የአማራ ክልል ደኅንነትና የፀጥታ ካውንስል የጋራ ውሳኔ አሳልፏል።

የካውንስሉን ውሳኔ በሚያንፀባርቀው መግለጫው ላይ እንደተገለፀው፤ በተለይ ከመስከረም 15 ቀን 2012 ዓ.ም. ጀምሮ በአካባቢው በተፈጠረ ግጭት ከፍተኛ ጉዳት ደርሷል።

የክልሉና የፌዴራሉ መንግሥት ለግጭቱ መንሥኤ ናቸው በተባሉት ጉዳዮች ላይ በሠለጠነ መንገድ ምላሽ መሥጠታቸውን ያስታወሰው ይኽው መግለጫ፤ ጥረታቸው ውጤት ሳያመጣ መቅረቱን አልሸሸገም። በቅርቡ ግን እየተፈፀመ ያለው ተግባር ክልሉን ወዳላስፈላጊ ትርምስ ሊከት እንደሚችል፣ ለክልሉም ኾነ ለመላው አገሪቱ የፀጥታ ስጋት ወደመኾን መሸጋገሩን ካውንስሉ ባወጣው መግለጫ ጠቁሟል።

የሰው ሕይወትና ንብረት በየቀኑ እየጠፋ በመኾኑ፤ ይህንን ችግር ወደሰላም ለመመለስ የፌዴራል መንግሥት ጣልቃ እንደገባና በውሳኔም መሠረት በአካባቢው ተፈፃሚ የሚኾኑ መመሪያዎችን ደንግጓል።

መመሪያው የተለያዩ ይዘቶችና በአስገዳጅነት ተፈፃሚ የሚኾኑ ያላቸውን ድንጋጌዎችንም በዝርዝር አስቀምጧል። የመመሪያውን ሙሉ ቃል ለማንበብ እዚህ ይጫኑ! (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ