Happy Ethiopian Newy Year! መልካም አዲስ ዓመት ይሁንልዎ!

EZEMA

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ)

“ተከብቤአለሁ” በማለት ለደረሰው ጥፋት መነሻ ከኾነው ግለሰብ ጀምሮ አደጋ ያደረሱት በሙሉ ለፍርድ ይቅረቡ! (ኢዜማ)

ኢዛ (ማክሰኞ ጥቅምት ፲፰ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. October 29, 2019)፦ በአገር መረጋጋት፣ ሰላም፣ እንዲሁም ከቀጣሁ ምርጫ ጋር ተያይዞ ባሉ አንገብጋቢ ጉዳዮች ላይ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ያሳተፈ ውይይት በፍጥነት መጀመር እንዳለበት ኢዜማ አሳሰበ። ለሰሞኑ ብጥብጥ፣ የዜጎች ሕይወት መጥፋትና ንብረት መውደም መነሻ ከኾነው ከጃዋር ጀምሮ አደጋው ያደረሱት በሙሉ ለፍርድ ይቅረቡ ሲል ኢዜማ ጠይቋል።

ኢዜማ ይህንን ያስታወቀው በወቅታዊ የአገሪቱ ጉዳዮች ዙሪያ፤ በተለይም ሰሞኑን በኦሮሚያ የተለያዩ ከተሞች ከተከሠተው አሳዛኝ ድርጊትን በማስመልከት ዛሬ በሠጠው መግለጫ ነው።

“የኢትዮጵያ ሕዝብ ለቀረበለት አገርን የማዳን ጥሪ በሕብረት መልስ መሥጠት የሚገባው ወቅት ዛሬ ነው” በሚል ባወጣው መግለጫ፤ ከወቅታዊ የአገሪቱ ሁኔታ ጋር በተያያዘ መፈጸም አለባቸው ብሎ ያመነባቸውን ዋና ዋና ጉዳዮች በዚሁ መግለጫ አካትቱቅል። በተለይ በሰሞኑ ድርጊት ልብ የሚነካ መኾኑንና ጥቅምት 13 እና 14 ለደረሰው ጥፋት መነሻ ከሆነው “ተከብቤአለሁ” በሚል መረጃ ከረጨው ግለሰብ ጀምሮ በየደረጃው በሰው ሕይወትና ንብረት ላይ አደጋ ያደረሱ ሰዎች በሙሉ ለፍርድ እንዲቀርቡ ጠይቋል።

“ተከብቤአለሁ” በማለት በፌስቡክ የማኅበራዊ ገጹ ላይ ጥቅምት 13 ቀን ንጋት ላይ መልእክት የረጨረጨው ግለሰብ አክቲቪስት ጃዋር መሐመድ እንደኾነ ይታወቃል። የመግለጫውን ሙሉ ቃል ለማንበብ እዚህ ይጫኑ! (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ዜና እና ፖለቲካ

ኪነ-ጥበብ

ቪዲዮ

መጻሕፍት

ስለእኛ

ይከተሉን!