ያልተገመተው ውጤት

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ኮትዲቯርን ሁለት ለአንድ ረታ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ኮትዲቯርን 2ለ1 አሸነፈ
ኢዛ (ማክሰኞ ኅዳር ፱ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. November 19, 2019)፦ በተደጋጋሚ ሽንፈት ሲወቀስ የነበረው የኢትዮጵያ ብሔራዊ የእግር ኳስ ቡድን በአፍሪካ ኃያል ከሚባሉ ቡድኖች አንዱ የኾነውን የኮትዲቯርን ቡድን ሁለት ለአንድ ረታ።
ለአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ዛሬ በባህር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም በተደረገው የሁለቱ አገሮች ግጥሚያ ኢትዮጵያ ያልተጠበቀ ድል ቀንቷታል።
በአውሮፓ ታላላቅ ክለቦች የሚጫወቱ ተጫዋቾችን ጭምር ያሰባሰበው የኮትዲቯር ቡድን በኢትዮጵያ የተሸነፈው በጨዋታ ጭምር ተበልጦ ነበር።
በቴሌቭዥንና በራዲዮ የተላለፈውን ይህንን ጨዋታ የተመለከቱ ደጋፊዎች የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ያሳየው ብቃት የተለየ መኾኑን ሲገልጹ ንበር።
ለአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ከአራት ቀናት በፊት ወደ ማዳጋስካር ተጉዞ የነበረው የኢትዮጵያ ቡድን በማዳጋስካር አንድ ለዜሮ ተሸንፎ ነበር። (ኢዛ)