Protest in Amhara region over student abductions, January 28, 2020

“እኅቶቻችን ይፈቱ!” በማለት በአማራ ክልል የተካሔደው ከፍተኛ ሰላማዊ ሰልፍ (ማክሰኞ ጥር ፲፱ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. January 28, 2020)

ተማሪዎቹ ለታገቱበት ክልል ለኦሮሞ ሕዝብ ጥሪ አስተላልፏል

ኢዛ (ማክሰኞ ጥር ፲፱ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. January 28, 2020)፦ በደንቢ ዶሎ ተማሪዎች ላይ በተፈጸመው እገታና ጥቃት በአማራና በአማራ ተወላጅ ተማሪዎች ላይ ብቻ ሳይሆን፤ በሰብዓዊ ፍጡርና በዜጐች ላይ መኾኑን በመገንዘብ፤ መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ በተለይም ጥቃቱ የተፈጸመበት ክልል የኦሮሞ ሕዝብ ከጐናችን ይቁም ሲል የአማራ ክልል ብሔራዊ ክልል መንግሥት ዛሬ ጥር 19 ቀን 2012 ዓ.ም. አስታወቀ።

የክልሉ መንግሥት ዛሬ ማምሻውን "የሕግ የበላይነትን በማጠናከር የዜጎችን ደኅንነት እናስጠብቃለን!" በሚል ርዕስ ባውጣው መግለጫ፤ የአማራ ክልል ሕዝብ በቀጣይም በተናጠልም ኾነ በቡድን በአማራ ክልል ተወላጆች ላይ የሚደርስን ጥቃት በሰላማዊ መንገድ ለመታገል ከመንግሥት ጎን ይቁምም ብሏል። የመግለጫውን ሙሉ ቃል ለማንበብ እዚህ ይጫኑ! (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ዜና እና ፖለቲካ

ኪነ-ጥበብ

ቪዲዮ

መጻሕፍት

ስለእኛ

ይከተሉን!