አቶ አገኘው ተሻገር እና አቶ ተመስገን ጥሩነህ

አዲሱ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አገኘው ተሻገር (ግራ) እና ኃላፊነታቸውን የለቀቁት አቶ ተመስገን ጥሩነህ (ቀኝ)

አዲሱ ተሿሚ አቶ አገኘው ተሻገር ናቸው

ኢዛ (እሁድ ጥቅምት ፳፱ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. November 8, 2020)፦ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር በመኾን ሲያገለግሉ የነበሩት አቶ ተመስገን ጥሩነህ ኃላፊነታቸውን ለቅቀው አዲስ ርዕሰ መስተዳድር ተመረጠ።

አቶ ተመስገን ጥሩነህ ኃላፊነታቸውን ለመልቀቅ ያቀረቡትን ጥያቄ የክልሉ ምክር ቤት ተቀብሏቸው፤ በምትካቸው የአማራ የብልጽግና ፕርቲ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ በመኾን ሲያገለግሉ የቆዩትን አቶ አገኘው ተሻገርን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አድርጎ የክልሉ ምክር ቤት ሾሟቸዋል።

አቶ ተመስገን ጥሩነህ ከኃላፊነታቸው የለቀቁት ለሌላ ኃላፊነት በመታጨታቸው መኾኑ ተገልጿል። አገሪቱ ካለችበት ወቅታዊ ሁኔታ አንጻር በተሰጣቸው ተልዕኮ ምክንያት መልቀቂያቸውን ማቅረባቸውን ለክልሉ ምክር ቤት ገልጸዋል።

ፓርቲያቸው በተሰለፈበት የአገር ማዳን ሥራ ላይ የሚጠበቅባቸውን ለማበርከት ስምሪቱን መቀበላቸውን ስለመግለጻቸውም ተመልክቷል። በአቶ ተመስገን ከኃላፊነት የመልቀቅ ጥያቄ ላይ ሰፊ ውይይት ከተደረገ በኋላ ጥያቄያቸውን ምክር ቤቱ ተቀብሏል። (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ዜና እና ፖለቲካ

ኪነ-ጥበብ

ቪዲዮ

መጻሕፍት

ስለእኛ

ይከተሉን!