ሌተናል ጄኔራል አስራት ዴኔሮ

የመከላከያ ሠራዊት መረጃ ዋና መምሪያ ኃላፊ ሌተናል ጄኔራል አስራት ዴኔሮ (ፎቶ፣ መከላከያ)

የጠቋሚዎች ማንነት የማይገለጽና በምስጢር እንደሚያዝ ተገልጿል

ኢዛ (ዓርብ ታኅሣሥ ፱ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. December 18, 2020)፦ የሕወሓት ጁንታ አመራሮች የሚገኙበትን ለጠቆመ ማንኛውም ዜጋ የ10 ሚሊዮን ብር ሽልማት የሚሰጥ መኾኑን የመከላከያ ሚኒስቴር አስታወቀ።

የመከላከያ ሠራዊት መረጃ ዋና መምሪያ ኃላፊ ሌተናል ጄኔራል አስራት ዴኔሮ ዛሬ ዓርብ ታኅሣሥ 9 ቀን 2013 ዓ.ም. እንደገለጹት፤ የጁንታውን አመራሮች በአጭር ጊዜ በቁጥጥር ሥር ለማዋል የሚደረገውን ጥረት ለማገዝ፤ ተቋማቸው የአሥር ሚሊዮን ብር ሽልማት ማዘጋጀቱን አስታውቀዋል።

ጥቆማውን የሚያደርጉ ግለሰቦች ማንነታቸው የማግይገለጽና በምስጢር የሚያዝ ሲሆን፤ ሽልማቱ በምስጢር የሚሰጣቸውና ደኅንነታቸው እንዲጠበቅ የሚደረግ መኾኑንም ተጠቁሟል።

የሚገኙበትን የሚያውቅ ማንኛውም ግለሰብ በአካባቢው ለሚገኘው የመከላከያ ሠራዊት በአካል በመቅረብ ወይም በመከላከያ ሠራዊት የስልክ ቁጥሮች (09 43 47 13 36 እና 012 5 50 43 48) መጠቆም እንደሚቻልም ተገልጿል። (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ዜና እና ፖለቲካ

ኪነ-ጥበብ

ቪዲዮ

መጻሕፍት

ስለእኛ

ይከተሉን!