National Election Board of Ethiopia (NEBE)

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ (ምርጫ 2013)

የድምፅ መስጠቱ ሒደት ሙሉ በሙሉ የተጠናቀቀባቸው ምርጫ ጣቢያዎች ተዘግተዋል

ኢዛ (ሰኞ ሰኔ ፲፬ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. June 21, 2021)፦ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የድምፅ መስጠት ሒደቱ እስከ ሦስት ሰዓት እንደሚቀጥል አስታወቀ።

በአንዳንድ የምርጫ ጣቢያዎች የድምፅ አሰጣጥ ሒደቱ ሙሉ በሙሉ መጠናቀቁንና ምርጫ ጣቢያዎች መዘጋታቸውን ገልጾ፤ ነገር ግን ምርጫ 2013 ያልተጠናቀቀባቸው ጣቢያዎች እስከ ሦስት ሰዓት ይቀጥላሉ ብሏል።

ከተፎካካሪ ፓርቲዎች ውስጥ የመጀመሪያውን መግለጫ የሰጠው ኢዜማ፤ ምርጫው ዘግይቶ የተጀመረባቸው ቦታዎች ሰዓት እንዲጨመር ጠይቆ እንደነበር መዘገባችን ይታወሳል። (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ