Abebech Gobena

ወ/ሮ አበበች ጎበና ከሚያሳድጓቸው ልጆች ጋር

በኮሮና ምክንያት በጳውሎስ ሆስፒታል ላለፉት ሁለት ወራት ሕክምና ሲከታተሉ ቆይተው ነበር

ኢዛ (እሁድ ሰኔ ፳፯ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. July 4, 2021)፦ በበጎ አድራጎት ተግባራቸው የሚታወቁትና “የብዙዎች እናት” በሚል የሚወደሱት ወይዘሮ አበበች ጎበና ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ።

በኮቪድ 19 (ኮሮና ቫይረስ) ተይዘው ባለፉት ሁለት ወራት በጳውሎስ ሆስፒታል ሕክምናቸውን ሲከታተሉ የቆዩት ወይዘሮ አበበች ሕይወታቸው ለሊት 11 ሰዓት አካባቢ አልፏል።

በበጎ አድራጎት ተግባራቸው ከ40 ዓመታት በላይ በበጎ አድራጎት ተግባራቸው ላበረከቱት አስተዋጽኦ የክብር ዶክትሬት የተጎናጸፉት አበበች ጎበና፤ “የአፍሪካ ማዘር ቴሬዛ” እስከመባል የደረሱ ነበሩ። (ኢዛ)

ስለ ወ/ሮ አበበች ጎበና ከተለያዩ የማኅበራዊ ገጾች ላይ የተሰበሰቡ ፎቶግራፎች
ስለ ወ/ሮ አበበች ጎበና ከተለያዩ የማኅበራዊ ገጾች ላይ የተሰበሰቡ ፎቶግራፎች

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ