Grand Ethiopian Renaissance Dam (GERD)

የታላቁ ህዳሴ ግድብ ሁለተኛ ዙር የውኃ ሙሌት ተጀመረ

ኢትዮጵያ በአቋሟ ጸንታ ቅጥላለች

ኢዛ (ማክሰኞ ሰኔ ፳፱ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. July 6, 2021)፦ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ሁለተኛው ዙር የውኃ ሙሌት መጀመሩ እየተነገረ ነው። የግብጽ የመስኖ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤት ለግብጽ መገናኛ ብዙኃን እንደገለጸው ከኾነ፤ ኢትዮጵያ ለግብጽ በኦፊሴል ሁለተኛውን ዙር የውኃ ሙሌት መሙላት መጀመርዋን አስታውቃላች።

የውኃ ሙሌቱን መጀመር በይፋ ከኢትዮጵያ መንግሥት ማረጋገጫ ባይሰጥበትም፤ የግብጽ ባለሥልጣናት ከኢትዮጵያ ወገን የውኃ ሙሌቱ መጀመሩን አሳውቀውናል ብለዋል።

ኢትዮጵያ ሁለተኛውን የውኃ ሙሌት በተያዘለት ጊዜ እንደምታካሒድ ደጋግማ ያስታወቀች ሲሆን፤ ግብጽ እና ሱዳን ግን ከእኛ እውቅና ውጭ የሙሌት ሥራው አይጀመር ብለው በመወትወት ጉዳዩን እስከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ለማድረስ ሞክረው ነበር።

ኢትዮጵያ ግን በአቋሟ ጸንታ የግድብ ሥራውን ከማፋጠን ባሻገር በያዝነው ክረምት ሁለተኛ የውኃ ሙሌቱን እያካሔደት ነው። (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ