Ambassador Redwan Hussein

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን

በሰብአዊ እርዳታ ስም ለሕወሓት ቡድን መሣሪያ ለማስታጠቅ የሚደረጉ ሙከራዎች መኖራቸው ተገለጸ

ኢዛ (ሐሙስ ሐምሌ ፰ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. July 15, 2021)፦ በእርዳታ ስም ወደ ኢትዮጵያ ገብተው፤ በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ የሚገቡ አካላትን መንግሥት የማይታገስ እና የአሸባሪው የሕወሓት ቡድን ሕፃናትን ለውትድርና እየማገደ መኾኑን እያዩ ዓለም አቀፍ ተቋማት ነገሩን በአወንታ መመልከታቸው ፍጹም ተቀባይነት እንደማይኖረው የኢትዮጵያ መንግሥት ገለጸ።

በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን በኩል የተገለጸው የኢትዮጵያ መንግሥት አቋም የሚያመለክተው መግለጫ፤ በተለይ በሰብአዊ እርዳታ ስም የሽብር ቡድኑን መሣሪያ ለማስታጠቅ የሚደረጉ ሙከራዎች መኖራቸውን እና መንግሥት በሰጠው የጥሞና ጊዜ ለውጥ የማይኖር ከኾነ፤ አገር የማዳን ውሳኔውን ደግሞ የሚያየው መኾኑን አሳውቋል።

የኢትዮጵያ መንግሥት ከውጭና ከውስጥ በተቀናጀ ሁኔታ በሚፈጸምበት አሻጥር አገር ስትፈርስ ዝም ብሎ እንደማይመለከት ያመለከቱት አምባሳደሩ፤ በእርዳታ ስም ወደ ኢትዮጵያ ገብተው በውስጥ ጉዳይ ጣልቃ የሚገቡ አካላትንም የማይታገስ መኾኑን ነው።

አምባሳደሩ በዛሬው መግለጫቸው ካመላከቱዋቸው ጉዳዮች ውስጥ፤ የሽብር ቡድኑ ሕፃናትን በውትድርና ማሳለፉና ለዚህም ዓለም አቀፍ ተቋማት ዝምታን የሚመለከት ነው።

በዚህ ጉዳይ በሰጡት ማብራሪያ አሸባሪው ቡድን በዓለም አቀፍ ሕግ የተወገዘውን የሕፃናት ለውትድርና የማሰለፍ ተግባሩ አሁንም እንደቀጠለ መኾኑን ጠቅሰው፤ ይህንን ተግባር ዓለም አቀፍ ተቋማት በአወንታ መመልከታቸው ፍጹም ተቀባይነት የሌለው መኾኑን ነው። (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ዜና እና ፖለቲካ

ኪነ-ጥበብ

ቪዲዮ

መጻሕፍት

ስለእኛ

ይከተሉን!