Ethiopia Zare (ቅዳሜ መጋቢት 6 ቀን 2000 ዓ.ም. March 15,2008) የዶላር ምንዛሬ በከፍተኛ ሁኔታ መናር ምክንያቱ በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ የጥቁር ገበያ የዶላር መመንዘሪያ ሱቆች ናቸው በሚል ፖሊስ የመመንዘሪያ ቦታዎችን መቆጣጠሩ ተዘገበ። በአካባቢው መውጣትና መግባት አይቻልም።

 

በተለይ በከፍተኛ ሁኔታ ምንዛሬ የሚደረግባቸው በፍልውሀ፣ ግዮን፣ ጋንዲ፣ መርካቶ፣ ካሳንችስና ሌሎች ቦታዎች የሚገኙ የዶላር መመንዘሪያ ሱቆች በፖሊስ ተከበው በቪዲዮ እየተቀረጹ የዋሉ ሲሆን፣ ሕጋዊ ባልሆነ መንገድ በአዲስ አበባና ዋና ዋና ከተሞች በርካታ ገንዘብ በመበተኑ የዶላር ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ ለመጨመሩ ምክንያት ሆኗል በሚል አካባቢዎቹ በፖሊስ እየተመረመሩ መሆኑን ለማወቅ ችለናል።

 

‘የኢኮኖሚውን ሁኔታ አገዛዙ በቅጡ ለማስያዝ ባለመቻሉ ምክንያት የተፈጠረውን ችግር በንግዱ ማኅበረሰብ ላይ ለመለጠፍ የሚደረግ ተራ ማደናገር ነው’ ሲሉ አስተያየታቸውን የሰጡ ታዛቢ፤ ‘የኢህአዴግ መንግሥት ለጨው መጨመር - ነጋዴ፣ ለስኳር ዋጋ መናር - ነጋዴ፣ ለጋዝ ዋጋ ጭማሪ ምክንያቱ - ነጋዴ፣ ለማኪያቶና ለሳሙና ዋጋ ተጠያቂ ነጋዴው ከሆነ፤ የመንግሥቱ ድርሻ ምን ሊሆን ነው?’ ካሉ በኋላ ‘መፍትሄው አንድና አንድ ነው፤ እሱም የአስተዳደር ችግርን ከሀገሪቱ ለማስወገድ ቆርጦ መነሳት ብቃት ያላቸው ባለሙያዎችን ማሰማራት ነው’ በማለት አስተያየታቸውን ደምድመዋል።

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ