Ethiopian banks

የኢትዮጵያ ባንኮች

ኢዛ (ዓርብ መስከረም ፳፫ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. October 4, 2019):- በኢትዮጵያ ውስጥ የሚንቀሳቀሱ የግልና የመንግሥት ባንኮች ዓመታዊ ትርፋቸው እየጨመረ መሆኑንና በ2011 ዓ.ም. ባንኮቹ ከግብር በፊት ከ32 ቢሊዮን ብር በላይ እንደደረሰ ተጠቆመ።

የባንኮቹን እንቅስቃሴዎች የሚያመለክቱ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት ከኢትዮጵያ ልማት ባንክ ውጭ ያሉት 17ቱም ባንኮች ዓመታዊ ትርፋቸው እያደገ መጥቷል።

ከ17ቱ ባንኮች አንዱ በመንግሥት ባለቤትነት የሚተዳደረው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሲሆን፣ 16ቱ የግል ባንኮች ናቸው። በ2011 ባንኮቹ ከታክስ በፊት እንዳስመዘገቡ ከተገለፀው ከ32 ቢሊዮን ብር በላይ ትልቁን ድርሻ የያዘው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ነው።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በቅርቡ ባወጣው መግለጫ በ2011 በጀት ዓመት ከግብር በፊት ያገኘው ትርፍ 17.9 ቢሊዮን ብር ነው። ቀሪዎቹ 16 የግል ባንኮች ደግሞ፤ በመጀመሪያ ደረጃ የኦዲት ሪፖርታቸው በድምር ያስመዘገቡት ትርፍ ደግሞ ከ14 ቢሊዮን ብር በላይ መሆኑን የሚያሳይ ነው።

ይህም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን ጨምሮ 17ቱም ባንኮች በጥቅል ከግብር በፊት ያስመዘገቡት ትርፍ በ2010 በጀት ዓመት ጋር ሲነፃፀር በ2011 ዓመት ያገኙት ትርፍ ከ10 ቢሊዮን ብር በላይ ብልጫ አለው። (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ዜና እና ፖለቲካ

ኪነ-ጥበብ

ቪዲዮ

መጻሕፍት

ስለእኛ

ይከተሉን!