ብርጋዲየር ጄኔራል ተፈራ ማሞና ኮሎኔል አለበል አማረ

ብርጋዲየር ጄኔራል ተፈራ ማሞና ኮሎኔል አለበል አማረ

በ15ቱ ግድያ ስለመሳተፋቸው መረጃ አልተገኘም

ኢዛ (ሐሙስ ታኅሣሥ ፱ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. December 19, 2019)፦ ሰኔ 15 ቀን 2011 ዓ.ም. የአማራ ክልል ከፍተኛ ባለሥልጣናትን በመግደል ወይም ከገዳዮች ጋር በአባሪ ተባባሪነት ተጠርጥረው ተከሰው የነበሩን የክልሉ ከፍተኛ የጦር መኮንኖች ፍርድ ቤት በነፃ አሰናበታቸው።

ጉዳዩን ሲመለከት የነበረው የአማራ ጠቅላይ ፍርድ ቤት እነዚህን የክልሉ ባለሥልጣናት የነበሩትን ተከሳሾች ከተመሠረተባቸው ክስ ነፃ ኾነው በነፃ መሰናበታቸውን የሚያረጋግጠውን ውሳኔ የሠጠው ትናንት ታኅሣሥ 8 ቀን 2012 ዓ.ም. ነው።

በነፃ የተሰናበቱት እነዚህ የቀድሞዎቹ የአማራ ክልል የፀጥታ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ብርጋዲየር ጄኔራል ተፈራ ማሞ፣ ኮሎኔል አለበል አማረ፤ ኮሎኔል በአምላክ ተስፋና ኮማንደር ጌትነት ሺፈራው ናቸው። ባለሥልጣናቱ በተጠረጠሩበት የወንጀል ክስ ታስረው ከአንድ ወር ተኩል በፊት ከእስር ተለቀው ነበር። ተከሳሾች በዋስ ከተፈቱ በኋላም ሲከራከሩ ቆይተዋል።

የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ግን በአራቱ ተከሳሾች ላይ የመሠረተውን ክስ የሚያጠናክር የሰውም ኾነ የቴክኒክ ማስረጃ ባለመገኘቱ፤ አራቱም በነፃ እንዲሰናበቱ ሊወስን መቻሉ ታውቋል። (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ዜና እና ፖለቲካ

ኪነ-ጥበብ

ቪዲዮ

መጻሕፍት

ስለእኛ

ይከተሉን!