የአማራ ብሔራዊ ክልል መስተዳድር ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ

የአማራ ብሔራዊ ክልል መስተዳድር ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ

123ቱ ሴቶች ናቸው

ኢዛ (ማክሰኞ መጋቢት ፳፪ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. March 31, 2020)፦ የአማራ ክልላዊ መንግሥት 7 ሺህ 650 ለሚኾኑ የሕግ ታራሚዎች ይቅርታ በማድረግ ከእስር እንዲፈቱ ወሰነ። የክልሉ መንግሥት ይህንን ውሳኔ ያስተላለፈው ከኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከል እንደኾነ ታውቋል።

የክልሉ ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ በይቅርታ እንዲፈቱ ውሳኔ ከተላለፈላቸው ታራሚዎች ውስጥ 7 ሺሕ 527 ወንዶችና 123 ሴቶች መኾናቸውን አስታውቋል።

ከሰው መግደል ውጭ በሌሎች ወንጀሎች ተፈርዶባቸው በእስር የሚገኙ፤ የሚያጠቡ እናቶች፣ የመፈቻ ጊዜያቸው አንድ ዓመት የቀራቸውና ቀላል ወንጀል በመፈጸም ተፈርዶባቸው አንድ ዓመት የቀራቸው ታራሚዎች ይህንን እድል አግኝተዋል።

የውጭ ዜጎችም ከእስር እንዲፈቱ ውሳኔ የተላለፈ ሲሆን፤ እነዚህ ይቅርታውን ያገኙት የውጭ ዜጎች ግን ከሰው መግደል ውጭ ባሉ ወንጀሎች ታስረው የነበሩትን የሚመለከት እንደኾነ ታውቋል። (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ