የአቶ ልደቱ የዋስትና ጥያቄ ውድቅ ኾነ

አቶ ልደቱ አያሌው
ዓቃቤ የ14 ቀን ክስ መመሥረቻ ጊዜ ተሰጠው
ኢዛ (ዓርብ ነኀሴ ፳፱ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. September 4, 2020)፦ አቶ ልደቱ አያሌው በሌላ መዝገብ በቀረበባቸው ክስ ለቢሾፍቱ (ለደብረዘይት) ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት ያቀረቡት የዋስትና ጥያቄ ውድቅ ተደርገባቸው።
አቶ ልደቱ ዛሬ ዓርብ ነኀሴ 29 ቀነ 2012 ዓ.ም. በድጋሚ ያቀረቡት የዋስትና ጥያቄ ውድቅ የተደረገው፤ በተከፈተባቸው የክስ መዝገብ ዓቃቤ ሕግ ክስ ለመመሥረት የ14 ቀን ጊዜ ጠይቆ ስለተፈቀደለት ነው።
በዚህ ውሳኔ መሠረት ክስ እስኪመሠረት ድረስ በፖሊስ ጣቢያ እንዲቆዩ ፍርድ ቤቱ አዝዟል። ከዛሬው የፍርድ ቤት ውሎ በኋላ ኢዴፓ እንዳስታወቀው፤ የአቶ ልደቱን ጉዳይ አሁን በሚታይበት ሁኔታ ማስቀጠል ስለማይቻል፤ ጉዳዩን በፌዴራል ደረጃ እንዲታይና አካልን ነፃ የማውጣት ጥያቄ እንደሚያቀርብ አስታውቋል። (ኢዛ)