Bahirdar Ginbot 20 Airport

ባሕር ዳር ግንቦት 20 ኤርፖርት

በአዲስ ስያሜ እንዲጠራ አራት ምርጫዎች ቀርበዋል

ኢዛ (ሰኞ ጥቅምት ፲፮ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. October 26, 2020)፦ “ባሕር ዳር ግንቦት 20 ኤርፖርት” በሚል ሲጠራ የቆየው የባሕር ዳር አውሮፕላን ማረፊያ በአዲስ ስያሜ እንዲጠራ ተወሰነ።

ከክልሉ መንግሥት የወጣው መረጃ የአውሮፕላን ማረፊያው ስያሜ በቅርቡ ተለውጦ በአዲሱ ስያሜው እንዲጠራ ይደረጋል።

በዚህ የስያሜ ለውጥ ዙሪያ የአማራ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ዛሬ ሰኞ ጥቅምት 16 ቀን 2013 ዓ.ም. እንዳስታወቀውም፤ እስካሁን አውሮፕላን ማረፊያው ሲጠራበት የነበረው ስያሜ በቅርቡ እንደሚቀየርና ለአዲሱ ስያሜም የሚኾን እንደመነሻ አራት አማራጮችን አቅርቧል።

ለአውሮፕላን ማረፊያው አዲሱ ስያሜው እንደመነሻ የቀረቡት “ባሕር ዳር”፣ “በላይ ዘለቀ”፣ “ዓባይ” እና “ጣና” ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ የሚሉ ናቸው።

በእነዚህ አማራጮች ላይ ሕብረተሰቡ አስተያየት እንዲሰጥበትም ጥሪ አስተላልፏል። ይህንንም ጥሪ ያስተላለፈው የአውሮፕላን ማረፊያውን ስያሜ ለመቀየር ከሕዝብ አስተያየት መቀበል አስፈላጊ በመኾኑ እንደኾነ ቢሮው አስታውቋል።

የአውሮፕላን ማረፊያው ስያሜ እንዲለወጥ ከተወሰነባቸው ምክንያቶች ውስጥ ዋነኛው በስያሜው ውስጥ የተካተተው “ግንቦት 20” የሚለውን ለማስቀረት ነው። (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ዜና እና ፖለቲካ

ኪነ-ጥበብ

ቪዲዮ

መጻሕፍት

ስለእኛ

ይከተሉን!