የእስር ማዛዣ ከወጣባቸው 76ቱ የጦር መኮንኖች ውስጥ በምስሉ ላይ ያሉት 36ቱ ናቸው

የእስር ማዛዣ ከወጣባቸው 76ቱ የጦር መኮንኖች ውስጥ በምስሉ ላይ ያሉት 36ቱ ናቸው

መኮንኖቹ በአገር ክህደት ወንጀል የተጠረጠሩ ናቸው
14 ጄኔራሎች፣ 58 ኮሎኔሎች፣ አንድ ሻለቃና 3 ሻምበሎች መኾናቸው ታውቋል

ኢዛ (ረቡዕ ኅዳር ፱ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. November 18, 2020)፦ የአገር ክህደት በፈጸሙ 76 ጄኔራሎች መኮንኖች ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖችና የበታች ሹማምንቶች ላይ የፍርድ ቤት ማዘዣ ትእዛዝ የወጣባቸው መኾኑን የፌዴራል ፖሊስ አስታውቋል።

ዛሬ የፍርድ ቤት ትእዛዝ ከወጣባቸው 76ቱ ውስጥ 14ቱ ሜጀር ጄኔራሎችና ብርጋዲየር ጄኔራሎች ሲሆኑ፤ 58ቱ ደግሞ ኮሎኔሎች (47ቱ ኮሎኔሎች፣ 11ዱ ሌተናል ኮሎኔሎች)፤ አንድ ሻለቃ እና 3ቱ የሻምበልነት ማዕረግ ያላቸው ናቸው።

የፌዴራል ፖሊስ ዛሬ ረቡዕ ኅዳር 9 ቀን 2013 ዓ.ም. እንዳስታወቀው፤ እነዚህ ከፍተኛ የጦር መኮንኖች በሥራ ላይ ያሉና ጡረታ የወጡ ሲሆን፤ ከሕወሓት ጁንታ ቡድን ጋር በመኾን የአገር ሕልውናን አደጋ ላይ በመጣልና ሕገ መንግሥቱንና ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓቱን በኃይል በመናድ ወንጀል በመሳተፍ የሚፈለጉ ናቸው ያላቸውን 76 ተጠርጣሪዎች ስምም ይፋ አድርጓል።

በዚህ በያዝነው ወር ኅዳር 3 ቀን 2013 ዓ.ም. 64 ከፍተኛ የሕወሓት አመራሮችና 32 የጦር መኮንኖች ላይ የእስር ማዘዣ መውጣቱ አይዘነጋም። የፍርድ ቤት ማዛዣ የወጣባቸውን 76 ከፍተኛ መኮንኖችና የበታች ሹማምንትን በተመለከተ ፌዴራል ፖሊስ ያወጣው ማዕረግና ስም ዝርዝር የሚከተለው ነው። (ኢዛ)

1. ሜጀር ጄኔራል ማህሾ በየነ
2. ሜጀር ጄኔራል መሐመድ አይሻ ዘይኑ
3. ሜጀር ጄኔራል ሙሉ ግርማይ ገ/ሕይወት
4. ሜጀር ጄኔራል ሀለፎም እጂጉ
5. ብርጋዲየር ጄኔራል ፍትዊ ፀሐዬ ገ/እግዚአብሔር
6. ብርጋዲየር ጄኔራል ግደይ ኃይሉ ገ/እግዚአብሔር
7. ብርጋዲየር ጄኔራል ነጋሽ ዳኘው
8. ብርጋዲየር ጄኔራል መብራቱ ወ/አረጋይ
9. ብርጋዲየር ጄኔራል ወልደ ጊዮርጊስ
10. ብርጋዲየር ጄኔራል አብዲሳ ፍላንሳ
11. ብርጋዲየር ጄኔራል ጉሽ ገብሬ
12. ብርጋዲየር ጄኔራል ከበደ ፍቃዱ
13. ብርጋዲየር ጄኔራል ገብረጊዮርጊስ
14. ብርጋዲየር ጄኔራል ህንፃ ወ/ገወርጊስ
15. ኮሎኔል ተወልደ ገ/ትንሳይ
16. ኮሎኔል ንጉሤ ገብሩ
17. ኮሎኔል መብራቱ አሰፋ /አልማዝ/
18. ኮሎኔል ዘገየ ንጉሥ
19. ኮሎኔል ያለም
20. ኮሎኔል መብራቱ ተድላ
21. ኮሎኔል ነጋሽ መብራቱ
22. ኮሎኔል ተክሉ በላይ
23. ኮሎኔል ጥጋቡ መለስ
24. ኮሎኔል ግርማ ተካ
25. ኮሎኔል ሙሉጌታ ገብረክርስቶስ ነጋሽ
26. ኮሎኔል አራሞ ገ/መድህን
27. ኮሎኔል ተስፋዬ ገ/መድህን
28. ኮሎኔል ግርማል አለማየሁ
29. ኮሎኔል ነጋሽ አለፎም
30. ኮሎኔል ተስፋዬ ምሩፅ
31. ኮሎኔል ካሳየ አሰፋ
32. ኮሎኔል ነጋሲ ታደሰ ስዩም
33. ኮሎኔል ኪሮስ ሓጎስ ገ/ዝጋብሔር
34. ኮሎኔል ሙርፅ ገብረሊባኖስ አብርሃ
35. ኮሎኔል ኃ/ሥላሴ ኪሮስ ተስፋይ
36. ኮሎኔል ምሩፅ በርሔ/ተወርወር/
37. ኮሎኔል ኃይለሥላሴ አሰፋ
38. ኮሎኔል ደርበው ሀጎስ
39. ኮሎኔል ወልዴ ሀጎስ
40. ኮሎኔል ንጉሤ አማረ
41. ኮሎኔል ነጋሲ ታደሰ
42. ኮሎኔል ባራኪ /ወዲ ራያ/
43. ኮሎኔል ከበደ ገ/ሚካኤል
44. ኮሎኔል ፀጋ ብርሃን ገ/እዜር
45. ኮሎኔል ዘሩ ኃ/መለኮት
46. ኮሎኔል ኃይለ መዝገብ
47. ኮሎኔል አርኣያ ገብሩ ግደይ
48. ኮሎኔል የማነ ገ/ሚካኤል
49. ኮሎኔል ዘሩ መረሳ
50. ኮሎኔል ልጃለም ገ/ሕይወት
51. ኮሎኔል አስመላሽ ወልዴ
52. ኮሎኔል ፍሰሀ ግደይ
53. ኮሎኔል አምባቸው ወ/ገብርኤል
54. ኮሎኔል ገብረመስቀል ወልደገብርኤል
55. ኮሎኔል ወልዱሀጎስ ገብሩ
56. ኮሎኔል ገ/ሚካኤል ሀጎስ
57. ኮሎኔል ስብሀቱ መብራቱ
58. ኮሎኔል ጣሰው ወ/ጊዮርጊስ
59. ኮሎኔል ገ/እግዚያብሔር ዓለምሰገድ
60. ኮሎኔል ነጋሲ ታደሰ
61. ኮሎኔል ተክለ በላይ
62. ሌተናል ኮሎኔል ተወልደ አብርሃ ወ/ሚካኤል
63. ሌተናል ኮሎኔል ሙዘይ ተሰማ ስዩም
64. ሌተናል ኮሎኔል ሀዲሽ ገብረፃድቅ አለማየሁ
65. ሌተናል ኮሎኔል ፍስሃ በየነ ገ/ኪዳን
66. ሌተናል ኮሎኔል ምሩፅ ወ/አረጋይ ገ/መስቀል
67. ሌተናል ኮሎኔል ሙሩፅ በርሀ ኣበራ
68. ሌተናል ኮሎኔል ፀሐዬ ሀጎስ
69. ሌተናል ኮሎኔል ሀጎስ ኪሮስ
70. ሌተናል ኮሎኔል ገብረ ህንፃ ሀዲሽ
71. ሌተናል ኮሎኔል ገብረመድህን ወ/ማርያም አሉላ
72. ሌተናል ኮሎኔል ፈለቀ አይጠገብ
73. ሻለቃ አስገዶም መስፍን
74. ሻምበል ባሻ ሙእዝ መልካም
75. ሻምበል አርኣያ ተ/ኃይማኖት
76. ሻምበል ተስፋ ሕይወት ናቸው።

አዲስ ቪዲዮ

ዜና እና ፖለቲካ

ኪነ-ጥበብ

ቪዲዮ

መጻሕፍት

ስለእኛ

ይከተሉን!