National Election Board of Ethiopia (NEBE)

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ

ምርጫ ቦርድ ከፖለቲካ ፓርቲዎች ከፍተኛ አመራሮች ጋር በምርጫው ዙሪያ መከረ

ኢዛ (ሐሙስ የካቲት ፬ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. February 11, 2021)፦ ለስድስተኛው አገር አቀፍ ምርጫ ለእጩዎች ምዝገባ የሚያገለግሉ ሰነዶችና ቁሳቁሶች በትናንትው ዕለት (ረቡዕ የካቲት 3 ቀን 2013 ዓ.ም.) ማሠራጨት እንደጀመረ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ።

ቦርዱ ከፖለቲካ ፓርቲዎች ከፍተኛ አመራሮች ጋር በስድስተኛው አገራዊ ምርጫ ዙሪያ መክሯል።

በዚህ ወቅት ቦርዱ እንዳስታወቀው፤ ለምርጫ እጩዎች፣ ለመራጮችና ለድምፅ አሰጣጥ የሚያገለግሉ ሰነዶችና ቁሳቁሰች ዝግጅት ተጠናቋል። ሰነዶቹና ቁሳቁሶቹ የሚሠራጩት በሦስት ምዕራፍ ተከፋፍሎ መኾኑን ያስታወቀው ቦርዱ፤ ለእጩዎች ምዝገባ የሚያገለግሉ ሰነዶችና ቁሳቁሶች ከትናንት ጀምሮ መሠራጨት እንደሚጀምሩ አመልክቷል።

ለመራጮች ምዝገባና ለድምፅ አሰጣጥ የሚያገለገሉ ሰነዶችና ቁሳቁሶችም በቀጣይ እንደሚሠራጩም ገልጿል።

የየብስ፣ የአየርና ሌሎች የመጓጓዣ ዘዴዎች በመጠቀም የሥርጭት ሥራው እንደሚከናወን አስታውቆ፤ “ሥርጭቱን በክልልና በዞን ደረጃ ያሉ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቶች ከምርጫ ጣቢያ አስፈጻሚዎች ጋር በመኾን ያከናውኑታል” ብሏል።

በሥርጭት ወቅት በጉዞና በሚቀመጥበት ቦታ አስፈላጊውን ጥበቃ ለማድረግ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመነጋገር ዝግጅት መደረጉም ተጠቁሟል። በአሁኑ ወቅት የትግራይ ክልልን ሳይጨምር 673 የምርጫ ጣቢያዎች በመላ አገሪቱ ይገኛሉ። የዞንና የምርጫ ክልል ጽሕፈት ቤቶች በክልሎች መክፈታቸውን ከቦርዱ የተገኘው መረጃ ያሳያል ሲል ኢዜአ ዘግቧል። (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ