Happy Ethiopian Newy Year! መልካም አዲስ ዓመት ይሁንልዎ!

Bank of Abyssinia

አቢሲንያ ባንክ

ካለፈው በጀት ዓመት በእጥፍ እንዳተረፈ ታውቋል

ኢዛ (ቅዳሜ ሐምሌ ፫ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. July 10, 2021)፦ አቢሲንያ ባንክ በ2013 በጀት ዓመት ከቀረጥና ከሌሎች ተቀናሾች በፊት 2.8 (ሁለት ነጥብ ስምንት) ቢሊዮን ብር ማትረፉን ባወጣው መግለጫ ገልጿል።

ባንኩ ባወጣው መግለጫ በአንድ ዓመት ውስጥ የሰበሰበው ተቀማጭ ገንዘብ ደግሞ 41 ቢሊዮን ብር እንደኾነና ይህም አጠቃላይ የተቀማጭ ገንዘብ መጠኑ ከ88 ቢሊዮን ብር በላይ እንደደረሰ አመልክቷል።

በተለይ የዘንድሮ ትርፉ በ2012 በጀት ዓመት ካገኘው ከእጥፍ በላይ እንደኾነ ለማወቅ ተችሏል።

የባንኩን ገንዘብ አስቀማጭ ደንበኞቹን ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩን ያመለከተው የአቢሲንያ ባንክ መግለጫ በበጀት ዓመት መጨረሻ ላይ የባንክ ደብተር ከፍተው ገንዘብ እያስቀመጡ ያሉ ደንበኞቹ ቁጥር 5.1 (አምስት ነጥብ አንድ) ሚሊዮን ደርሷል። (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ዜና እና ፖለቲካ

ኪነ-ጥበብ

ቪዲዮ

መጻሕፍት

ስለእኛ

ይከተሉን!