ወንድማገኘሁ ነገራ

የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ወንድማገኘሁ ነገራ

258 ሚሊዮን ብር ማትረፉንም ገልጿል

ኢዛ (ሐሙስ ሐምሌ ፰ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. July 15, 2021)፦ የኢትዮጵያ ምርት ገበያ በ2013 በጀት ዓመት 614,586 ሜትሪክ ቶን የተለያዩ ምርቶችን በ39.6 (በሠላሳ ዘጠኝ ነጥብ ስድስት) ቢሊዮን ብር ማገበያየቱን አስታወቀ።

የምርት ገበያው ዛሬ (ሐሙስ ሐምሌ 8 ቀን 2013 ዓ.ም.) በሰጠው መግለጫ እንዳስታወቀው፤ በበጀት ዓመቱ አገበያያለሁ ብሎ ካቀደው 96 በመቶውን ማሳካት ሲችል በገንዘብ መጠን ደግሞ ማሳካት የቻለው 102 በመቶ መኾኑን ገልጿል። የዛሬውን መግለጫ የሰጡት የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ወንድማገኘሁ ነገራ ናቸው።

በበጀት ዓመቱ ከተገበየው ምርት ውስጥ ቡና 35.5 (ሠላሳ አምስት ነጥብ አምስት) በመቶ፣ ሰሊጥ 31 በመቶ በመኾን ቀዳሚውን ሥፍራ ይዘዋል። ሌሎች የጥራጥሬ ምርቶች ደግሞ 33.4 (ሠላሳ ሦስት ነጥብ አራት) በመቶ ድርሻ እንደነበራቸው አስታውቋል።

በኢትዮጵያ ምርት ገበያ ካካሔደው ግብይት ኮምሽንና ከሌሎች የገቢ ምንጮች በአጠቃላይ 775 ሚሊዮን ብር ገቢ ያገኘ ሲሆን፤ ከወጪ ቀሪ ከቀረጥ በፊት 258 ሚሊዮን ብር ትርፍ አግኝቷል። (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ዜና እና ፖለቲካ

ኪነ-ጥበብ

ቪዲዮ

መጻሕፍት

ስለእኛ

ይከተሉን!