ሙስጠፌ መሐመድ

የሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ መሐመድ

የክልሎች ልዩ ኃይል በቦታው እየደረሱ ነው

ኢዛ (ዓርብ ሐምሌ ፱ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. July 16, 2021)፦ አገር ለማፍረስ የመጣውን ኃይል በሕብረት ከመታገል ውጪ አማራጭ የሌለ መኾኑን እና የሕወሓትን የሽብር ቡድን ጥቃት ለመከላከል የሶማሌ ክልል የጸጥታ ኃይል ወደ ግንባር ለመላክ ዝግጅት እየተደረገ መኾኑ ተገለጸ። ክልሎች የጸጥታ ኃይሎቻቸውን እየላኩ ነው።

የሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ መሐመድ እንደገለጹት፤ አገር ለማፍረስ የመጣውን ይህንን ኃይል ከመመከት ውጪ አማራጭ የሌለ በመኾኑ፤ ይህንንም በጋራ በመኾን መወጣት እንደሚገባም አመልክተዋል።

ቡድኑ ለትግራይ ሕዝብ ክብርና ኀዘኔታ ቢኖረው ኖሮ፤ በሌሎች ክልሎች ላይ ዳግመኛ ትንኮሳ ባላደረገም ነበር ብለው፤ ቡድኑ በአፋርና በአማራ ክልሎች ላይ ትንኮሳ ማካሔዱ አጀንዳው ኢትዮጵያን የማፍረስ እንደኾነ በግልጽ የሚያሳይ መኾኑንም አቶ ሙስጠፌ ገልጸዋል።

ከሶማሌ ክልል ቀደም ብሎ አሸባሪ ቡድኑ እያደረገ ያለውን ትንኮሳና ጥቃት በሕብረት ለመመከት እስካሁን የደቡብ፣ የሲዳማ እና የኦሮሚያ ክልሎች ልዩ ኃይሎች ወደ ግንባር መንቀሳቀሳቸው ይታወሳል።

በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ የክልል መስተዳድሮች የሕወሓት ቡድን እየፈጸመ ያለው ጥቃት ኢትዮጵያን ለመከፋፈል ያለመ በመኾኑ ክልሎች በጋራ ተባብረው ጥቃቱን ለመከላከልና የቡድኑን ምኞት ለመቀልበስ ሁሉም የበኩላቸውን ለማድረግ ዝግጁ መኾናቸውን እያሳወቁ ነው።

የሕወሓት ቡድን ከቀናት በፊት ተቆጣጥሬያቸዋለሁ ያላቸውን አንዳንድ ከተሞች በአሁኑ ጊዜ ከቡድኑ ነፃ መኾናቸው ይታወቃል። (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ