Dr. Desalegne Chane

የአብን ምክትል ፕሬዝዳንት ዶክተር ደሳለኝ ጫኔ

47,083 ድምፅ አግኝተው ነው ያሸነፉት

ኢዛ (ሰኞ ሰኔ ፳፰ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. July 5, 2021)፦ በአማራ ክልል በባሕር ዳር ከተማ የምርጫ ክልል ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተወዳደሩት የአብን ምክትል ፕሬዝዳንት ዶክተር ደሳለኝ ጫኔ አሸናፊ መኾናቸውን ምርጫ ቦርድ አረጋገጠ።

ዛሬ ሰኞ ሰኔ 28 ቀን 2013 ዓ.ም. ይፋ እየተደረገ ካለው የተረጋገጠ የምርጫ ውጤት ውስጥ ከተወዳደሩት ፓርቲዎች አሸናፊ መኾናቸው የተገለጸው የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄው (የአብኑ) ዶ/ር ደሳለኝ፤ አሸናፊ የኾኑት 47,083 ድምፅ በማግኘት ነው። ከእርሳቸው ቀጥሎ ከፍተኛ ድምፅ ያገኙት ተወዳዳሪ ደግሞ 35,133 ድምፅ ማግኘታቸውን ምርጫ ቦርድ ያመለከተ ሲሆን፤ በሁለቱ ተፎካካሪዎች መካከል ያለው የድምፅ ልዩነት 12,350 ነው።

በባሕር ዳር ከተማ የምርጫ ክልል ሰባት የፖለቲካ ፓርቲዎች እጩዎቻቸውን አቅርበው ነበር። እነርሱም ገዥው ፓርቲ ብልጽግና አንዱ ሲሆን፤ ከተፎካካሪ ፓርቲዎች ውስጥ አብን፣ ኢዜማ፣ እናት ፓርቲ፣ የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጀት፣ ኅብር ኢትዮጵያ፣ የኢትዮጵያ ነፃነት ፓርቲ፣ ነፃነትና እኩልነት ፓርቲ እና የአማራ ዴሞክራሲያዊ ኃይል ንቅናቄ ናቸው።

በዚህ የምርጫ ክልል 144 የምርጫ ጣቢያዎች የነበሩ ሲሆን፤ ለመምረጥ የተመዘገቡት ደግሞ 137,084 መራጮች ናቸው። (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ