የብልጽግና ፓርቲ ረቂቅ መተዳደሪያ ደንብ ማርሽ ቀያሪ አንቀጾች

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active
Critic on Prosperity party regulations

"አጋሮች ድሮውንም ከ4 ኪሎና ከመቀሌ በቀጭን ሽቦ በምትተላለፍ ትእዛዝ ጉዳያቸውን ሲፈጽሙና ሲያስፈጽሙ ስለሰነበቱ፣ አዲስ ነገር እንደማይሆንባቸውና አግኝተው ያጡት መብት ብዙም ፍንትው ብሎ ስለማይታያቸው፤ አዲሱን የድርጅታዊ አወቃቀር ሊቀበሉት ይችላሉ" ራሚደስ

በAddis Standard ድረገጽ የተለጠፈው የብልጽግና ፓርቲ ረቂቅ መተዳደሪያ ደንብ ያቃጨለው ደውል ቀላል የማይባልና ላለፉት ሦስት አሥርት ዓመታት ገደማ ኢሕአዴጋዊው የኢትዮጵያ አገረ መንግሥት ግንባታ ፕሮጀክት ሥር ነቀል ለውጥ የሚያስከትል መኾኑን ያበሰረ ወይንም ያረዳ ነው። ይህ ረቂቅ በኢሕአዴግ እኅት ድርጅቶችና በግንባሩ ጠቅላላ ጉባዔ ጸድቆ ወደ ተግባር መግባት ከቻለ የኢትዮጵያ ፌደራሊዝም ቢያንስ በወረቀት ላይ ሰፍሮ ከሚገኘው ያልተማከለ አስተዳደር ወደ ኢሠፓ መሰል የተማከለ አስተዳደር አስፈንጥሮ እንደሚያስገባው እሙን ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ብሔር፣ መንግሥትና ሕዝብ - የፖለቲካ ግብ ማሳለጫ ግንዛቤነታቸው

የአንባብያን ድምፅ: 4 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Inactive

"የአዋሳ ከተማ፣ የሐረር ከተማ፣ የድሬዳዋ ከተማ፣ የአዲስ አበባ ከተማ፣ ሌሎችም ትልልቅ ከተሞችና የንግድ ማዕከሎች፤ የመተላለቂያ ቦታዎች ከመሆን አይድኑም"

አንዱ ዓለም ተፈራ

አገራችን አሁን ያለችበት የፖለቲካ ቀውስ፤ ሥር መነሻ አለው። ይህ ቀውስ ትክክለኛ መፍትሔ እንዲያገኝና የተጀመረው የለውጥ ሂደት ግቡን እንዲመታ፤ መሠረታዊ የሆኑ የሕብረተሰባችን ግንዛቤዎቻችን ሊለውጡና፤ በአመራሩም በኩል ተገቢ የፖለቲካ እርምጃዎች ሊወሰዱ ይገባቸዋል። ያለው ሐቅ፤ ላለፉት ሃያ ሰባት ዓመታት በትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር (ሕወሓት) መንግሥት ሲካሄድ የነበረው ዕልቂት፤ አሁንም በየቦታው ቀጥሎ መጧጧፉ ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

“ኩኩሉ …” ማለት ይቻላል አይደል? (በፍቃዱ ሞረዳ)

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active
Jawar Mohammed

“ለሁሉም በሚበጅ ጉዳይ ላይ ተቀራርቦ ያለመታከት መነጋገር ያስፈልጋል፤ በግራ እጅ እየካቡ በቀኝ መናድ ኪሳራ ነው - በፍቃዱ ሞረዳ (ጋዜጠኛ)

የውጭ አገር ዜግነት ባላቸው ሰዎች የሚተዳደሩ ሚዲያዎችን አስመልክቶ ዐቢይ አሕመድ ለኢሕአዴግ ፓርላማ ያሰሙትን ንግግር/ዛቻ፣ አንዳንድ ቅን ልቦች "ጃዋርን የሚመለከት አይደለም" እያሉ ሊያረጋጉ እየሞከሩ ነው። "እንደአፋችሁ ያድርግልን" እንላለን።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የመደመር መጽሐፍ ምረቃ - የዘገምተኞችና አድር ባዮች ጭብጨባ በሚሌኒየም

የአንባብያን ድምፅ: 4 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Inactive
ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ የመደመር መጽሐፍ ምርቃት ላይ ፊርማ ሲያኖሩ

“በርግጥ ሰውዬውም ጭብጨባ ይወዳል”

አምባቸው ደጀኔ (ከወልዲያ)

ጥቅምት 8 ቀን 2012 ዓ.ም. - የዶ/ር ዐቢይ መጽሐፍ ተመርቋል። እኔም ከዚያ በተያያዘ ራሴን ታምሜ ዋልኩ - አሁን ድረስ። የነበረኝ የEmotional Quotient አንጻራዊ የተሻለ ደረጃ ወርዶብኝ ራሴው ስቸገርና ሰዎችንም ሳስቸግር አመሸሁ። የሚገነዘብህ ሰው ሲጠፋ ራስህን ያምሃል፤ ሲያምህ ሁሉም ነገር ያስጠላሃል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የኦርቶዶክስንና አማራን አከርካሪ የመምታት የመጨረሻው ምዕራፍ

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋኅዶ ፓትርያርኮች

“ኦርቶዶክስም አሁን ለምትገኝበት የነፍስ ውጪ ነፍስ ግቢ አሳሳቢ ደረጃ የደረሰችው የራሷን የመታነቂያ ገመድ ራሷው ፈትላ ነው”

ምሕረት ዘገዬ

1. የጠ/ሚንስትሩ የመደመር ልቦለድ መጽሐፍ እየተመረቀ ባለበት በአሁኑ ቅጽበት በአዲስ አበባና በዙሪያዋ ምን እየተደረገ ነው?

  • መዝገብ የያዙና በሥውር የፖሊስ ኃይል ጥበቃ የሚደረግላቸው የወለጋና አርሲ ቄሮዎች በጀሞና በሌሎች የአዲስ አበባ ከተማ ሕጋዊ ይዞታዎች ሥር የሚገኙ መሬቶችን እየተከፋፈሉ ነው። ካለበቂ ጥበቃ የሚገኙ ኮንዶሚኒየሞችን በር በመስበርም እየተሻሙ ነው። እነሱን ሃይ የሚል ግሕግ የለም። …
  • የሌሎች ዜጎች በተለይም የአማሮች ቀደምት ይዞታዎች በሻማና በኩራዝ እየታሰሱ እንዲፈርሱና ሰዎቹ ወደው ባልተፈጠሩበት ነገዳቸው ምክንያት ማቄን ጨርቄን ሳይሉ ከቦታቸውና ከአገራቸው እንዲፈናቀሉ እንዲሰደዱም እየተደረገ ነው - በአዲስ አበባ ዙሪያ ሁሉ። …
  • አማሮች ከያዟቸው የፌዴራልና የክልል ሥልጣንና ኃላፊነቶች እየተነሱ የገዢው ኃይል ታማኝ የሆኑ ሆዳሞችና ምሥጢረኞች እንዲሁም የአማራን መጠሪያ ስሞችና የአማራነትን ዘውጋዊ የውሸት ማንነት በዳግም ጥምቀት ያገኙ አሰለጦች እየተተኩ ነው። አማራ በቋንቋውም ሆነ በባህሉ ለማንምና ለሁሉም እኩል ክፍት በመሆኑ ይህ ሁኔታው ክፉኛ እያስጠቃው ይገኛል። በተቅጠፈጠፈ አፉና በአስመሳይ ኢትዮጵያዊ የሥነ ልቦና ቀመሩ ሠርጎ የሚገባ ዘረኛ ሁላ፤ አማራን በቀላሉ ለጥቃት ይዳርገዋልና ለዚህ ዐይነቱ ችግር አፋጣኝ መፍትሔ ካልተገኘ ችግራችን እንደጠነነ መቀጠሉ ነው። ለዚህም አንዱ ምሣሌ ከአማራ ሕዝብና አዴፓ አባላት ጋር ውኃና ዘይት የሆነው የጠሚው ልዑክ - ስሙም ጠፋኝ - የአማራው ክልል አዲስ ፕሬዝዳንት ነው። ይህ ሰው መንፈስ ቢጤ ሳይሆን አይቀርም። የት ነው ያለው ግን? ምን እየሠራስ ነው? ዋና ተልእኮው ለጠሚው ነው ወይንስ ለአማራ? የዘር ሐረጉ የሆነውን ይሁን ግዴለም - ግን ለክልሉ ምን እየፈየደ ነው? በፍንጭ ሰጭ ቃላት ጉግል አድርጌ ስሙን አሁን አገኘሁት - እውነቴን ነው - ተመስገን ጥሩነህ። ወይ መሪና ተመሪ! ተለያየን።
ሙሉውን አስነብበኝ ...

እውነትም ስምን መላክ ያወጣዋል - ደጀን ከተማና አካባቢዋ ያሳዩት ኢትዮጵያዊነት!

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active
ከዓርብ መስከረም 30 ቀን 2012 ዓ.ም. ከረፋድ ጀምሮ በኦሮሚያ ክልል ጎሐጽዮን አካባቢ ቄሮዎችና የኦሮምያ ፖሊስ መንገድ ዘጉ

ግርማ በላይ

የአንዳንድ ስያሜዎች እውናዊ ልጨኛነት የሚገርም ነው - የአንዳንዶች ደግሞ ከማስገረምም አልፎ በለበጣ የሚያስፈግግ ነው። “ዐመለ ወርቅ” ተብላ ነጭናጫ፣ “ሽመክት” ተብሎ ባንድ ጥፊ የሚዘረር፣ “ደም መላሽ” ተብሎ ከእናትና አባቱ ገዳይ ጋር በጎን ተመሳጥሮ ባንድ መሸታ ቤት አሥረሽ ምቺው የሚል ወስላታ፣ … የመኖሩን ያህል፤ እንደስማቸው “አለልኝ”ና “ድጋፌ” ሆነው ለተመካባቸው ሰው ደጀንና ከለላ የሚሆኑ ድንቅ ዜጎች አሉ። እርግጥ ነው ስም አይገዛምና በስም ዙሪያ ብዙ ተቃራኒ ነገሮች መኖራቸው እውነት ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ዜና እና ፖለቲካ

ኪነ-ጥበብ

ቪዲዮ

መጻሕፍት

ስለእኛ

ይከተሉን!