አብርሃም በየነ

ጭብጥ ጥሬ በልቶ

ጥርኝ ውኃ ጠጥቶ

ኖርኩ እንዲልም ኑሮ

የደከመ አካሉን መደብ ላይ ዘርሮ፤

የበሽታ ቀለብ የሞት ስንቅ መኖ

የረሃብ ከረጢት አይጠግቤ ለምኖ፤

እጆቹን ዘርግቶ አንጋጦ ወደ ላይ

ተመስገን ጌታዬ ይህን አታሳጣኝ

ለሚል ምጿተኛ ልቡ ደምቶ አዶናይ፤

ቸርነት ካልቸረው መድኃኒዓለም ደጉ

ማተብ ያስበጥሳል ድርጊተ-ፈለጉ።


አብርሃም በየነ (ሚያዝያ 2008)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ