Commissioner General Endeshaw Tasew

የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጄኔራል እንዳሻው ጣሰው

ፖሊስ በሁሉም የአዲስ አበባ መግቢያዎች ጥበት ቁጥጥር እየተደረገ ነው
ፖሊስ ከመስከረም 25 በኋላ መንግሥት የለም የሚሉት ላይ እርምጃ እወስዳለሁ አለ

ኢዛ (ዓርብ መስከረም ፲፭ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. September 25, 2020)፦ ፌዴራል ፖሊስ በአራቱም የአዲስ አበባ መግቢያ በሮ ጥብቅ ፍተሻ እያካሔደ መኾኑንና በአዲስ አበባ የሽብር ድርጊት ለመፈጸም ዝግጅት ላይ እንዳሉ እንደደረሰበትም አስታውቋል።

የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጄኔራል እንዳሻው ጣሰው በሰጡት መግለጫ ሽብር ለመፍጠር በዝግጅት ላይ እንዳሉ ስለተደረሰበትም ወደ አዲስ አበባ በሚያስገቡ በሁሉም በሮች ላይ ጥብቅ ፍተሻ እየተደረገ ስለመኾኑም ገልጸዋል።

የደመራ መስቀል በዓልና የኢሬቻ በዓልን አከባበርና የፖሊስ ዝግጅትን አስመልክተው በሰጡት በዚሁ መግለጫ፤ በዓላቱን በሰላም ለማክበር ፖሊስ ከሕብረተሰቡ ጋር በመኾን እየሠራ መኾኑንም ገልጸዋል።

የመስቀል ደመራ እና የኢሬቻ በዓላትን ሰላማዊ በኾነ መንገድ እንዳይከበር ለማድረግ የሚንቀሳቀሱ ኃይሎች ስለመኖራቸውም በመጥቀስ፤ ፖሊስ በዓላቱ በሰላም እንዲጠናቀቁም በቂ ዝግጅት አድርጎ ወደ ሥራ መግባቱንም ተናግረዋል።

ከዚህም ሌላ ከመስከረም 25 ቀን 2013 ዓ.ም. በኋላ መንግሥት የለም በሚል ሕዝብ ለአመጽ እንዲነሳሳ የሚያደርጉ መልእክቶችን በስፋት የሚያሰራጩ እንዳሉ በመጠቆም፤ እንዲህ ባለው ተግባር ላይ የሚሠማራ ማንኛውንም አካል የማይታገስና እርምጃ የሚወሰድ ስለመኾኑም አስጠንቅቀዋል። (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ