Turkey, Izmir bomb attack

ኢዛ (ኀሙስ ታህሳስ ፳፯ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም. Jan. 05, 2017)፦ በዛሬው ዕለት ኢዝሚር በተባለች የቱርክ ከተማ በፍርድ ቤት አቅራቢያ ሦስት ታጣቂዎች የሽብር ጥቃት ፈጸማቸውንና ሁለቱ ጥቃት ፈጻሚዎች፣ አንድ ፖሊስ እና አንድ የፍርድ ቤቱን ሠራተኛ መግደላቸውን የቱርክ የመንግሥት መገናኛ ብዙኀን ዘገቡ።

ጥቃቱ በመኪና ላይ በተጠመደ ቦምብ እና በመሳሪያ የተፈጸመ መሆኑን እና ከአራቱ ሟቾች በተጨማሪ አስር ሰዎች በከፍተኛ ሁኔታ መቁሰላቸው ተገልጧል።

ሦስተኛውን ጥቃት አድራሽ ከአካባቢው የተሰወረ ሲሆን፣ ፖሊስ አሰሳ ላይ እንደሆነ ዘገባው ያስረዳል።

የቱርክ ባለሥልጣናት ለዚህ ጥቃት ተጠያቂ ያደረጉት የኩርድ ሚሊሻዎችን መሆኑን ዘገባው አክሎ ግልጧል።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የቱርክ ትላልቅ ከተሞች በኢስላሚ ስቴት (IS) እና በኩርድ ሚሊሻዎች የጥቃት ዒላማ እየሆኑ መምጣታቸው ይታወቃል። ባለፈው ሣምንት በኢስታንቡል ከተማ በሚገኝ የምሽት ክበብ ውስጥ ፴፱ (39) መገደላቸው አይዘነጋም። የዛሬው ጥቃት የደረሰባት ኢዝሚር ከተማ በኢስታንቡሉ ጥቃት የተጠረጠሩ ሰዎች የሚገኙባት ከተማ ነች።

ቱርክ ባለፍው ዓመት ኦገስት ላይ የመከላከያ ኃይሏን በሶሪያ በማዝመት የኢስላሚክ ስቴትን እና የኩርድ ሚሊሻዎችን ከድንበሯ ለማሸሽ ሞክራ እንደነበር ይታወሳል።

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ