Gonder

ጎንደር ከተማ

የጁንታው ቡድን ሮኬቱን እንደተኮሰ በአቶ ጌታቸው ረዳ በኩል አስታውቋል

ኢዛ (ቅዳሜ ኅዳር ፭ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. November 14, 2020)፦ ትናንት ምሽቱ አምስት ሰዓት አካባቢ በጎንደር እና በባሕር ዳር ከተሞች ላይ የተተኮሰው ሮኬት መኾኑ ሲረጋገጥ፤ ይህንንም የጁንታው ቡድን ስለመፈጸሙ ተረጋግጧል።

ትናንት ምሽት ላይ በተተኮሰው ሮኬት በጎንደር አውሮፕላን ማረፊያ አካባቢ መጠነኛ ጉዳት መድረሱን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መረጃ መጣሪያ አስታውቋል።

በዚሁ ጉዳይ ላይ በተሰጠው ተጨማሪ መረጃ “ስግብግቡ ጁንታ በእጁ ያሉትን የመጨረሻዎቹን መሣሪያዎች ጠጋግኖ ሞክሯል” ብሏል።

ይህም ከመሞቱ በፊት የመጨረሻዎቹን አቅሙን እየሞከረ መኾኑን የገለጸው የመረጃ ማጣሪያው፤ ዝርዝሩ መርማሪ ቡድን ተመድቦ እያጣራ ሲሆን፤ በቀጣይ የሚገለጽ መኾኑንም የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መረጃ ማጣሪያ አስታውቋል።

የጁንታው ቡድን አመራር አቶ ጌታቸው ረዳ ደግሞ ሮኬቱን እነርሱ መተኮሳቸውን ለትግራይ ሚዲያ አረጋግጠዋል። አቶ ጌታቸው በትግርኛ ቋንቋ በሰጡት ቃለ ምልልስ በጎንደርና በባሕር ዳር ቡድናቸው ሕወሓት ጥቃቱን ማድረሱንና ይህንን የሮኬት ጥቃቱን እንደሚቀጥል ተናግረዋል። (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ