ጥያቄዎቻችን በጆሮ ዳባ ልበስ ሊታለፉ አይገባም!
ጥያቄዎቻችን በጆሮ ዳባ ልበስ ሊታለፉ አይገባም፤ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድና ገዢው ፓርቲ ተገደው እንዲሰሙ የማድረግ ህዝባዊ ትግል ይቀጥላል!!
ከ33ቱ የፔቲሽን ፈራሚ ፓርቲዎች ባቀረብነው ጥያቄ ዙሪያ በቀጣይ የጋራ አቋም ላይ የተሰጠ መግለጫ
1. መግቢያ
በአዳማ ከተማ በ2005 ምርጫ የጊዜ ሠሌዳ ላይ ለማወያየት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በሰበሰበን ወቅት ከተሣታፊ 66 ፓርቲዎች 41ዱ ከጊዜ ሠሌዳው በፊት የውድድር ሜዳውን መስተካከል በሚመለከቱ አበይት የምርጫ ጉዳዮች ልንወያይ ይገባል ከሚለው ኃሣብ በመነሣት እና በጉዳዩ ለመግፋት ፔቲሽን ፈረምን፡፡ በመቀጠልም በ29/02/05 ዓ.ም 18 ጥያቄዎችን ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ /ኢብምቦ/፣ 13 ጥያቄዎችን ደግሞ በ08/04/05 ለክቡር ጠቅላይ ሚ/ር ጽ/ቤት፣ ለህዝብ ተወካዮች ም/ቤት አፈጉባኤ ጽ/ቤት አቅርበን ከቦርዱ ጥያቄአችሁ “ውሃ አያነሳም” በሚል ሙሉ በሙሉ ውድቅ መደረጉ በ10/04/05 ዓ.ም በቃል ሲገለጽልን፤ ከጠቅላይ ሚ/ር ጽ/ቤት፣ ከህዝብ ተወካዮች ም/ቤት አፈጉባኤ ጽ/ቤት መልስ እየጠበቅን መሆኑን ገልጸን መልስ መጠባበቃችንን ቀጠልን።
ሙሉውን አስነብበኝ ...

ጥቅምት 15 ቀን 2005 ዓ.ም. በአዳማ ከተማ ፔቲሽን ተፈራርመው
የኢትዮጵያ ሕዝብ የጋራ ትግል ሸንጎ ኅዳር 5 ቀን 2005 ዓ.ም. (ኖቨምበር 14 ቀን 2012 እ.ኤ.አ.) የሸንጎው አመራር ካውንስል ባካሄደው መደበኛ ስብሰባው ላይ ያሳለፋቸውን ውሳኔዎች አስመልክቶ መግለጫ አውጥቷል። ሙሉው መግለጫ እንደሚከተለው ይነበባል።
ከአባይ ሚዲያ ዋና አዘጋጅ፣ 


