የአርቲስት ሐጫሉን ግድያ ተከትሎ በአገሪቱ በርካቶች ተገደሉ፣ ከፍተኛ ንብረት ወደመ

Hachalu Hundessa

በሐረር የራስ መኮንን፣ በሎንዶን የቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ሐውልቶች ፈርሰው ተሰባበሩ

ኢዛ (ማክሰኞ ሰኔ ፳፫ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. June 30, 2020)፦ የአርቲስት ሐጫሉ ሁንዴሳን ግድያ ተከትሎ ከትናንትና ምሽት ጀምሮ በተለይ በአዲስ አበባ አንዳንድ አካባቢዎች ተረብሸው ያደሩ ሲሆን፣ ንጋት ላይ ደግሞ አዲስ አበባን ጨምሮ በተለያዩ የኦሮሚያ ክልል ከተሞች በርካታ ሰዎች ሕይወታቸው ማለፉ ተነገረ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ኢዜማ የኢትዮ ቴሌኮምን ለመሸጥ የተጀመረው እንቅስቃሴ በአስቸኳይ እንዲቆመ ጠየቀ

Ethio Telecom

የሽያጭ ሒደቱ አደጋ አለው ብሏል

ኢዛ (ቅዳሜ ሰኔ ፳ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. June 27, 2020)፦ ገዥው ፓርቲ የኢትዮ ቴሌኮምን ከፊል ይዞታ ለመሸጥ እየሔደበት ያለውን ጥድፊያ በመኮነን ይህንን ጥድፊያ በአስቸኳይ እንዲቆም ጠየቀ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በሩዋንዳና በጅቡቲ ያሉ ወንጀለኞችን አሳልፎ ለመስጠት የሚያስችል አዋጅ ጸደቀ

Ethiopia, Djibouti and Rwanda

በሁለቱ አገራት ጥቂት ያልኾኑ በወንጀል የሚፈለጉ ኢትዮጵያውያኖች እንዳሉ ይነገራል

ኢዛ (ዓርብ ሰኔ ፲፱ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. June 26, 2020)፦ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ኢትዮጵያ ከጅቡቲና ከሩዋንዳ ጋር በወንጀል የሚፈለጉ ሰዎችን አሳልፎ ለመስጠት የሚያስችላቸው ረቂቅ አዋጅ አጸደቀ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የአምስት የእርቀ ሰላም ኮምሽን አባላት ሹመት ጸደቀ

House of Peoples' Representatives

ተሿሚዎቹ ቃለ መሃላ ፈጽመዋል

ኢዛ (ዓርብ ሰኔ ፲፱ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. June 26, 2020)፦ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ትናንት ሐሙስ ሰኔ 18 ቀን 2012 ዓ.ም ባካሔደው ስብሰባው የተጓደሉ የእርቀ ሰላም ኮሚሽን አባላት ሹመትን የተመለከተ ሲሆን፣ በዚህም በጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ የቀረቡለትን የተጓደሉ የእርቀ ሰላም ኮሚሽን አባላትን ለማሟላት አምስት አበላቶችን ሹመት አጽድቋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በኢትዮጵያ ግዙፉ የዳቦ ማምረቻ ተመርቆ ሥራ ጀመረ

ሸገር ዳቦ

9 ሚሊዮን ብር ወጪ ጠይቋል
በሰዓት 80 ሺህ፣ በቀን ሁለት ሚሊዮን ዳቦ የማምረት አቅም አለው

ኢዛ (ሐሙስ ሰኔ ፲፰ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. June 25, 2020)፦ ላለፉት አሥር ወራት በቅርብ ክትትል ሲገነባ የቆየው እና በሰዓት 80 ሺሕ ዳቦ የሚያመርተው የሸገር ዳቦ ዛሬ ሐሙስ ሰኔ 18 ቀን 2012 ዓ.ም. በጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ተመርቆ ሥራ ጀመረ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ኢሳይያስ አፈወርቂ ካርቱም ናቸው

President Isaias Afwerki and Sudan's President of Sovereign Council, LT-General, Abdul Fattah Al-Burhan

የኤርትራን እና የሱዳንን የሁለትዮሽ ትብብሮችን ማጠናከር በሚቻልባቸው ላይ ይመክራሉ

ኢዛ (ሐሙስ ሰኔ ፲፰ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. June 25, 2020)፦ የኤርትራ ፕሬዝዳንት ኢሳይያስ አፈወርቂ የሥራ ጉብኝት ለማድረግ ዛሬ ሐሙስ ሰኔ 18 ቀን 2012 ዓ.ም. ካርቱም ገብተዋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የኢትዮጵያ ፌዴራሊስት ኃይሎች ጥምረት ሕወሓትን ከአባልነት አገደ

Dereje Bekele

“ሕወሓት እና ኢዲዩ የጥምረቱን ጉዞ ለማደናቀፍ እና አገር ለማተራመስ እየሠሩ ነው” ጥምረቱ

ኢዛ (ሐሙስ ሰኔ ፲፰ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. June 25, 2020)፦ በሕወሓት አሰባሳቢነት የተደራጀ መኾኑ የሚነገርለት የኢትዮጵያ ፌዴራሊስት ኃይሎች ጥምረት፤ ሕወሓት እና ኢዲዩን ከአባልነት ማገዱን አስታወቀ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የትግራይ ክልል ምርጫ ለማድረግ ይረዳኛል ብሎ ያቀረበው ጥያቄ በምርጫ ቦርድ ውድቅ ተደረገ

ሕወሓት፣ ኮሮና እና ምርጫ ቦርድ

ቦርዱ ከትግራይ ክልል ምክር ቤት የተጠየቀውን የሰው ኃይል፣ የሎጄስቲክስ እና የቁሳቁስ አቅርቦት የሚሰጥበት የሕግ አግባብ አለመኖሩንም አሳውቋል

ኢዛ (ረቡዕ ሰኔ ፲፯ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. June 24, 2020)፦ የትግራይ ክልል ምክር ቤት በክልሉ ምርጫን ለማካሔድ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ያቀረበውን ጥያቄ ቦርዱ ውድቅ አደረገው። ቦርዱ ከትግራይ ክልል ምክር ቤት የተጠየቀውን የሰው ኃይል፣ የሎጄስቲክስ እና የቁሳቁስ አቅርቦት የሚሰጥበት የሕግ አግባብ አለመኖሩንም አሳውቋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አብን ባልተገባ መንገድ ወደ ትግራይ በተከለሉ አካባቢዎች ምርጫ እንዳይካሔድ ሊጠይቅ ነው

NAMN and TPLF

ባልተገባ መንገድ ወደ ትግራይ ክልል የተካለሉት እንደ ወልቃይት፣ ሑመራ፣ ራያ፣ ጠለምት እና የመሳሰሉት አካባቢዎች ላይ ነው እግዱን የሚጠይቀው

ኢዛ (ማክሰኞ ሰኔ ፲፮ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. June 23, 2020)፦ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ባልተገባ መንገድ ወደ ትግራይ ክልል የተከለሉ ናቸው ባላቸው አካባቢዎች ምርጫ እንዳይካሔድ የእግድ ጥያቄ ሊያቀርብ ስለመኾኑ ተገለጸ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ዜና እና ፖለቲካ

ኪነ-ጥበብ

ቪዲዮ

መጻሕፍት

ስለእኛ

ይከተሉን!