አዲስ አበባ በረራ ናት፤ በረራም አዲስ አበባ

የአንባብያን ድምፅ: 4 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Inactive

አምባ የጥናት እና ምርምር ክፍል ያቀረበው ጥናታዊ ጽሑፍ

Map of Barara and its surrounding.
Map of Barara and its surrounding. The places shown on the map and others are identified by Marco. From Marco Vigano, “The Names Lost, the Map Grasped,”

በሀቅ ላይ የተመሰረተ ታሪክ ጽኑ የአንድነት መሰረት ነው። ፍትህንም ለማስፈን ወሳኝ ሚና አለው። ታሪክ የራሱ የሆነ የሙያ ስነምግባር አለው። የታሪክ ባለሙያ ለሙያው ፍቅርም ሲል ህይወቱን መስዋዕት ለማድረግ ዝግጁ መሆን አለበት። የሚያስከፋም ሆነ የሚያስደስት፣ የሚያስነቅፍም ሆነ የሚያስወድስ በመረጃ የተመሰረተ ሀቀኛ ታሪክን መቀበል የስልጡንነት ምልክት ነው። ታሪክን መፍራት፣ መካድ እና ማድበስበስ ኋላቀርነት ነው። ታማኝ መረጃ እስከተገኘ ድረስ ታሪክ ያለምንም ገደብ ይጻፋል። ያስከፋል ወይም ያስነቅፋል ብሎ በታሪክ ላይ ሀጢያት መስራት ጉዳቱ ከባድ ነው። የታሪክ ዕውቀት ያድጋል፣ ይሰፋል ይቀየራል። ይህ የሚሆነው ደግሞ አዳዲስ መረጃዎች በአይነትና በመጠን ሲገኙ ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የፓትርያርክ አቡነ ቴዎፍሎስ የመጨረሻዎቹ ሰዓታት

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

አክሊሉ ሀብተወልድ

Patriarch of the Ethiopian Orthodox Tewahido Church Abuna Theophilos
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ፓትርያርክ የነበሩት አቡነ ቴዎፍሎስ

ሐምሌ 7 ቀን 1971 ዓ.ም. ዕለተ ቅዳሜ ከታላቁ ቤተ መንግሥት ምድር ቤት እስረኞች መካከል የክርስትና እምነት ተከታዮች የሆኑት በጠዋት ተነስተው በአባቶች መሪነት ጸሎት አድርሰዋል። የቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ደውል ድምፅ ሲያስተጋባ ሰምተዋል። ፈጣሪያቸውን አውቀው በድፍረት ሳያውቁ በስህተት የፈፀሙትን በደል ይቅር እንዲላቸው ተማጽነዋል። ከጸሎት በኋላ እስረኞቹ ጧት ፀሐይ ለመሞቅና አየር ለመቀበል የተፈቀደላቸው ለ45 ደቂቃ ጊዜ አጠናቀው ወደየክፍሎቻው ተመልሰው ተቆልፎባቸዋል። የሐምሌ ፀሐይ በቀዝቃዛው በታላቁ ቤተ መንግሥት ምድር ቤት ውስጥ የታጎሩትን ታላላቅ ኢትዮጵያውያን ለማጽናናት የተላከች ይመስላል፤ ሰማዩን በጋረደው ደመና መካከል ብልጭ ድርግም ትላለች።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የበላይ ዘለቀ ፎቶግራፍ

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

ዮፍታሔ

Belay Zeleke
በላይ ዘለቀ

የዘንድሮው የአርበኞች ቀን የስመ ጥሩው አርበኛ በላይ ዘለቀ ስም ጎልቶ እይታሰበ የተከበረበት መሆኑ ተጠቅሷል - ይልቁንም በአማራ ክልል።

ይህንን ተከትሎ ደግሞ ዶክተር ሽብሩ ተድላ “ከጉሬዛ ማርያም እስከ አዲስ አበባ የሕይወት ጉዞዬ እና ትዝታዬ” በሚል ርዕስ ያሳተሙትን መጽሐፍ በመጥቀስ ከዚህ በታች የሚታየው የበላይ ዘለቀ ፎቶ የርሱ እንዳልሆነ የሚገልጹ ጽሑፎች ወጥተው እያነበብን ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የጃንሆይ እናት

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

ዳዊት ከበደ ወየሳ - ከአትላንታ

Ras Darge Sahle Selassie
ራስ ዳርጌ ሣህለሥላሴ፣ የሸዋው ንጉሥ ሣህለሥላሴ ልጅ

ነገሩ ትንሽ ቆየ። እኔ ግን በሆነ አጋጣሚ በቅርቡ ነው ቃለ ምልልሱን የሰማሁት። ተስፋዬ ገብረአብ አዲስ ስላሳተመው - “የጀሚላ እናት” መጽሐፍ፤ ከጋዜጠኛ በፍቃዱ ሞረዳ ጋር አጭር ቃለምልልስ አድርጎ ነበር። በትክክል እንዳዳመጥነው ከሆነ፤ “የቀዳማዊ ኃይለሥላሴ እናት ስም ጀሚላ ነው፤ አንድ ወገናቸው ስልጤ ጉራጌ ነው - በሌላ ወገን ኦሮሞ ናቸው።” ይለናል። (ቃለምልልሱን ለመመልከት እዚህ ይጫኑ!)። በመቀጠልም፤ “የጀሚላ እናት በአቶ በዛብህ ተጠልፈው ነበር። አቶ በዛብህ ከምኒልክ ጋር በጦርነት ሞቱ። የቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ወይም የጀሚላ እናት እልፍኝ ውስጥ፤ በአፄ ምኒልክ ተገደሉ።” የሚሉና ሌሎች ተዘርዝረው የማያልቁ የልብወለድ ነገሮች በመጽሃፉ ውስጥ ማካተቱን በቃለ ምልልሱ ላይ ሰማን። ወደ ኋላ በመመለስ ‘በወቅቱ ምላሽ የሰጠ ሰው ይኖር ይሆን?’ በማለት አንዳንድ ድረ ገጾችን ብመለከት፤ በዚህ የተዛባ ታሪክ ምክንያት … “ኢትዮጵያ ሆይ ታሪክ ነጋሪ አጣሽ?” የሚሉ የቁጭት አስተያየቶችን አነበብኩ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አድዋ ለኛ የሚሰጠን ትርጉም ምንድን ነው? እኛስ ከአድዋና ከሌሎች አገሮችስ ምን ተማርን?

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

ፈቃዱ በቀለ (ዶ/ር)

The battle of Adwa.
የአድዋ ጦርነት የአፍሪካውያን ድል ነው!

 

መግቢያ

በአፄ ምኒልክና በተቀሩት ጀግና የጦር መሪዎቻቸው የሚመራው የኢትዮጵያ ወታደር በወራሪው ጣሊያን ላይ ድል ከተቀዳጀ ይኸው 121 ዓመት ሆነው። ከረጅም ዓመታት ጀምሮ የአድዋ በዓል በየአመቱ ይከበራል። በአሁኑ ወቅት ሁሉም ኢትዮጵያዊ ይህንን ታላቅ የድል በዓል ያከብራል። አገሩን ከሚወደውና አዲስ ኢትዮጵያን በጠንካራ መሰረት ላይ ለመገንባት ከሚፈልገው ጀምሮና፣ በማወቅም ሆነ ባለማወቅ ከውጭ ኃይሎች ጋር በማበር ዛሬ አገራችን የምናየው ውድቀት ውስጥ እንድትወድቅ ከፍተኛ አስተዋፅዖ ለማበርከት ከበቃው ድረስ፣ ሁሉም በየፊናው ይህንን በዓል ያከብራል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በአድዋ ጦርነት የመረጃ (Intelligence) ሚና

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

Adwa
አድዋ

በአገርና በሕዝብ ደህንነት ጥበቃ ሚኒስቴር ስር፤ ሐምሌ 1973 ዓ.ም. በታተመውና “ደህንነት” በተሰኘ መጽሔት ከገፅ 28 - 38 ከአድዋ ጦርነት በፊት፣ በጦርነቱ ጊዜና ከጦርነቱ በኋላ በጣሊያንና በኢትዮጵያ ወገን የተካሄደውን የስለላ ሥራ አስመልክቶ  “በአድዋ ጦርነት የኢንተለጀንስ ሚና” በሚል ርዕስ ስር የሚከተለውን ጽሁፍ አስፍሯል።

(መስቀሉ አየለ)

ሀ) የጠላት መረጃ

የኢጣሊያ መንግሥት ኢትዮጵያን ቅኝ ግዛቱ ለማድረግ ሲነሳ የራሱን ገንዘብና የወታደሮቹን ደም በብዛት ለማፍሰስ አልፈለገም። ኢትዮጵያን በቀላሉ ለመያዝ ይቻላል የማለት እምነት ያደረበት የኢትዮጵያን የፊውዳላዊ ፖለቲካ ጠባይ በእጅ አዙርም ሆነ በቀጥታ ከመገንዘቡ የተነሳ ነበር። የዒጣሊያ ተመራማሪዎች በብዛት ወደ ኢትዮጵያ ከመግባታቸው በፊት በአፄ ቴዎድሮስ ላይ የደረሰው ችግር ለኢጣሊያኖች ከፍተኛ ትምህርት ሆኗል። ኢጣሊያኖች በዝብዝ ካሳ (ዮሐንስ)፣ ዋግሹም ጎበዜና (ተክለጊዮርጊስ 2ኛ) የወሎ መኳንንት ቴዎድሮስን ባይክዱ፣ ለእንግሊዞች መንገድ ባያሳዩና ስንቅ ባይሰጡ ኖሮ የብሪታኒያ ሠራዊት መቅደላ ገብቶ ቴዎድሮስን ማሸነፍ ቀርቶ ላስታ እንኳን ለመድረስ በተሳነው ነበር ብለው አመኑ። ከቴዎድሮስ በኋላ በመሳፍንቱ መካከል ስለቀጠለው ሽኩቻና አለመግባባት በሰሜን ከ“ሳፔቶ”ና ከሌሎች ሚሲዮናዊያን የኢጣሊያ መንግሥት መረጃ ሲያገኝ በመሃልና ደቡብ አገር ደግሞ ኩማሳይና ከጭፍሮቹ እንዲሁም ከ“ነቼኪ” ብዙ ዕውቀት አግኝቷል። መጀመሪያ አሰብ ቀጥሎ ምፅዋ በኢጣሊያ እጅ ከገቡ በኋላ ደግሞ በስመ አገር ጎብኚዎችና ተመራማሪዎች ኢትዮጵያን በማጥለቅለቃቸው የኢጣሊያ መንግሥት ስለ አገሪቱ የፖለቲካ ሁኔታዎች ከኛ የበለጠ የሚያውቅ የለም ብሎ ተማመነ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

"ኢትዮጵያ" የሚለው ቃል ትርጉም

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

ገ/ኢ. ጐርፉ

The meaning of the name Ethiopia

“ኢትዮጵያ” የሚለው ቃል ትርጉሙንና አመጣጡን ለመመርመር በ፲፱፻፹፩ (1987 እ.ኤ.አ.) በወጣው ሰምና ወርቅ በተባለው የምርምር መጽሔት ፪ኛ ዓመት፣ ቁጥር ፬ አጥር ያለ ጽሑፍ አቅርበን፣ አንዳንድ ምሁራን፤ “ኢትዮጵያ ማለት ከግሪክ ቋንቋ የመጣ ቃል፣ ‘ፊቱ በፀሓይ የተቃጠለ፣ የተጠበሰ፣ ያረረ’ ማለት ነው ...” የሚሉት ትክክል እንዳልሆነ ለማሳየት፤ ናይጀርያ የሚባል አገርና፣ (Nigeria) ኒጀር (Niger) የሚባሉ አገርና ወንዝ በአፍሪካ እንዳሉ ጠቅሰን፣ ኔግራ፣ ኔግሮ፣ ኒገር፣ ኔግሪትዩድ (Negra, Negro, Nigger, Negritude) ለሚሏቸው ቃላት ወደ ላቲን/እንግሊዝኛ ቋንቋ ለመግባት ምክንያት ሆኑ እንጂ፣ ከላቲን ቋንቋ ተወስዶ ለአፍሪካ አገሮችና ወንዝ የተሰጠ ስም አይደለም በማለት፣ ኢትዮጵያ የሚለውም ቃል እንዲሁ ጥንታዊ ምንጩ ከግሪክ ሳይሆን ከአገራችን የወጣ ቃል መሆኑን ለመግለጽ ሞክረን ነበር።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ሆሣዕና በአርያም፤ ሆሣዕና ... ሆሣዕና... ሆሣዕና...!!

የአንባብያን ድምፅ: 4 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Inactive

ዲ/ን ክንፈ ገብርኤል
Hosaena

ሆሣዕና ቃሉ የዕብራይስጥ ሲሆን ትርጓሜውም "አሁን አድን" ማለት ነው። እንደ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እምነትና ሥርዓት ከፋሲካ/ከትንሳኤ በፊት ያለው እሑድ "የሆሣዕና እሑድ" በመባል ይታወቃል። በዚህ ዕለትም በቤተ ክርስቲያናችን የሚዘመረው መዝሙር፣ ማኅሌቱ፣ ቅዳሴው፣ ምንባቡና ማንኛውም አገልግሎት ሁሉ ዕለቱን በታላቅና እጅግ ደማቅ በሆነ መንፈሳዊ ሥነ - ሥርዓት የሚዘከርበት፣ የሚታሰብበት ነው። ይህ በዓል እጅግ በደማቅና ልብን በሚመስጥ መንፈሳዊ ሥነ-ሥርዓትና ድምቀት ከሚከበርባቸው ቅዱሳን ገዳማትና መካናት መካከል የአክሱሟ ርዕሰ አድባራት ጽዮን ማርያም እና በዚህ በአዲስ አበባችን የእንጦጦ ማርያም በዋናነት የሚጠቀሱ ናቸው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የአድዋ ድልና እኛ

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

ዳንኤል አበራ

1. መቅድም: ይህ የአድዋ 119ኛ አመት መታሰቢያ እኛና አድዋ በተሰኘ ርእሰ ጉዳይ ላይ ያተኩራል። ድርሰቱ ስድስት ንኡሳን ክፍሎች አሉት። ሁላችንም በጦርነቱ በድሉም ወቅት ስላልነበርን የተጻፈ አንብበን ከምናውቀው አመሳክረን ነው ጽሁፉ የተዘጋጀው። የተጻፈ አንብበን ላልኩት የጳውሎስ ኞኞን ምክር ከልቤ አድርጌ ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

እምዬ ምኒልክ!

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

የምኒልክ ሐውልትተመስገን ደሳለኝ (አዲስ አበባ)
ይህንን አጀንዳ ለማቅረብ ያሰብኩት ባለፈው ሳምንት ነበር፤ ይሁንና "የምስራቅ ኢትዮጵያ ፖለቲካ 2" የሚለው ፅሁፌ አንድም ወቅቱ "የብሔር ብሔረሰቦች ቀን" ዋዜማ በመሆኑ፣ ሁለትም በይደር የተላለፈው የዚሁ ተከታይ ፅሁፍ መቋጨት ግድ በማለቱ ነበር።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ዜና እና ፖለቲካ

ኪነ-ጥበብ

ቪዲዮ

መጻሕፍት

ስለእኛ

ይከተሉን!