የረቡዕ ግጥም ፬ኛ ዓመት፣ ቁ. ፳፯

ለምን ብለን
ውሸትን ቻል አ'ርገን
እንደ እርጎ ተግተን
እንደ ሱረት ምገን
ዝም ብለን ምናልፈው
ባለሥጣንን ነው
ፈርተን አጎብድደን
አንድም ለሆድ ብለን
ሙሉውን አስነብበኝ ...የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5
ውሸትን ቻል አ'ርገን
እንደ እርጎ ተግተን
እንደ ሱረት ምገን
ዝም ብለን ምናልፈው
ባለሥጣንን ነው
ፈርተን አጎብድደን
አንድም ለሆድ ብለን
ሙሉውን አስነብበኝ ...የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5
ፍቅርን ነበረ ይጓዛል እስከሞት
ብለን የምናውቀው ያነበብነው በፊት
ውሸትም እስከሞት ለካ አብሮ ይጓዛል
እንዲህ ያለ ተአምር በዚህ ዘመን ታይቷል
ሙሉውን አስነብበኝ ...የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5
ይኼ ኑሮ የምንለው
ሁለት ዐይነት ገጽታ አለው
አንድ ለ'ራስ
ለመንተራስ
አንድ ለአገር
ለመማገር
ሙሉውን አስነብበኝ ...የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5
ሰኔ ከሰኞ ጋር ገጠመ አልገጠመ
እማይመጣው መጥቶ ሚመጣው መቼ ቆመ
አሥሩ ቢወራ በዛ በዚህ ቢባል
የማይኾን አይኾንም የሚኾን ይኾናል
ሙሉውን አስነብበኝ ...የአንባብያን ድምፅ: 4 / 5
ቀሚስ ባይባልም አድርገሻል ቀሚስ
ጭፈራም ባይባል ተነስተሻል ለዳንስ
ዓይነ ግቡ ኾኖ ይታያል ቁመናሽ
ዓይቶ የማያልፈው ፈረደበት ያማሽ
ሙሉውን አስነብበኝ ...የአንባብያን ድምፅ: 4 / 5
ሐሳብና ስሜት አድርገው ሩጫ
ሐሳብ አሸንፎ ተቀበለ ዋንጫ
እንደዚሁ ሁሉ ሐሳብ የሌለው ሰው
ለጊዜው ቢሮጥም ሽንፈቱ ቅርብ ነው
ሙሉውን አስነብበኝ ...የአንባብያን ድምፅ: 4 / 5
ምን ዐይነት በሽታ መጣ በዚህ ዓመት
ቻይን አሜሪካ እግዜሩም ታሙበት
እግዜሩን እናውጣው የእኛ ነው ጥፋቱ
ጨክኖ አይጨክንም እሱ በፍጥረቱ
ሙሉውን አስነብበኝ ...የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5
በጣም ያሳስባል የአዳንድ ሰው ጉዳይ
ማበድ ጤንነቱ እንዴት ነው የሚለይ
እብድ ነው አይባል ደኅና ልብስ ለብሷል
ግን ደግሞ ሚሠራው ካበደው ይብሳል
ሙሉውን አስነብበኝ ...የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5
ኖርንበት እያልን እሱ እየኖረብን
አንድ አገር ብቻውን ሁለት ኾነብን
እልም ብሎ ጠፍቶ ያ ሁሉ በረዶ
ያደረ ይመስላል ሌላ አገር ተወልዶ
ሙሉውን አስነብበኝ ...የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5
ማየትን መስማትን ማሽተትን
በነፃ ሰጥቶን ፈጣሪያችን
ምስጋና ሳንሰጠው በበደል እዳችን
ያስከፍለን ጀመር ሕይወት በሳላችን
ሙሉውን አስነብበኝ ...